በወልዲያ ከተማ ለፖሊስ አባላት ሲሰጥ የነበረው የዲጂታል ወንጀል ጥቆማ ስልጠና ተጠናቀቀ።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ለሰሜን ወሎ ዞን እና ለወልዲያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አመራሮችና አባላት ሲሰጥ የነበረውን የ3 ቀን የዲጂታል ወንጀል ጥቆማና የመረጃ አሰባሰብ ስልጠና አጠናቋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ፈንታ ተጋፋው እንደገለጹት ስልጠናው ዘመኑን የዋጀ፣ ከልማዳዊ አሰራር የሚያላቅቅ እና ለህብረተሰቡ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት ምቹ መደላድል የፈጠረ ነው።

ፖሊስ ተቋምን ለማዘመን በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን በመግለጽ የህዝብ ተሳትፎ ጥቆማ መተግበሪያ አንዱ የዚሁ ማዘመኛ ስራ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል።

አዲሱ አሰራር ፖሊስ ቀልጣፋ እና ያልተደበቀ መረጃና ማስረጃን በቀላሉ በማግኘት ምርመራን በማጣራት ህግ ለማስከበርና ፍትህ ለማስፈን ምቹና ዘመናዊ መሆኑን ገልጸዋል።

የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር አበራ ካሳው በበኩላቸው ይህ መተግበሪያ ማህበረሰቡ ማንኛውንም የወንጀል አይነት ሲፈፀም በማንኛውም ስልክ በፎቶ፣ በቪድዮ፣ በድምፅ እና በፅሁፍ ጥቆማ ማሰጠት የሚያስችል ነው ብለዋል።

ማህበረሰቡ ያለምንም ስጋት በዘመናዊ መንገድ ጥቆማ በመስጠት ጊዜና ወጭን እንዲቆጥብ ያስችለዋል። ከዞን ስልጠና በኋላም ለወረዳ ፖሊስ አመራሮች፣ ለባለሙያዎች እና ለህብረተሰቡ ተጨማሪ ስልጠና በመስጠት ስራው በቅርብ ቀን ይጀመራል ብለዋል።

በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ ስልጠናውን ለሰጡት የክልሉ ፖሊስ አሰልጣኝ ምክትል ኢንስፔክተር ስብሃት ጥሩነህ የምስጋና እና የሽልማት ፕሮግራም የተደረገላቸው ሲሆን ለሚመጡ ጥቆማዎች ፈጣን ምላሽ በመስጠት ህዝቡን በቅንነት ለማገልገል አደራ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top