የ12ኛው ዓለም አቀፍ የጣና ፎረም ጉባኤ ሰላም መጠናቀቁ ተገለጸ።

የ12ኛው ዓለም አቀፍ የጣና ፎረም ጉባኤ ሰላም መጠናቀቁ ተገለጸ።

ከጥቅምት 13 እስከ 15/2019 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ ሲካሄድ የነበረው 12ኛው የጣና ዓለም አቀፍ የደህንነት ፎረም በሰላም መጠናቀቁን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

የፎረሙን ሰላማዊና ስኬታማ ፍጻሜ አስመልክቶ የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ባወጣው መግለጫ መርሃ ግብሩ በሰላም ተጠናቆ እንግዶች ወደ መጡበት እስኪመለሱ የተቀናጀ የፀጥታ ማስከበር ሥራ መከናወኑን ገልጿል ።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ከተለያዩ የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የተጠናከረ የጥበቃ፣ የትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር እና የቅድመ-ወንጀል መከላከል ሥራዎችን በትኩረት ሲያከናውን ቆይቷል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የክልሉ ፖሊስ እና የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች እንዲሁም የደህንነት ተቋማት ሌት ከቀን የላቀ ሙያዊ ዲስፕሊን በማሳየት ጉባኤው በሰላም እንዲጠናቀቅ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እና ላሳዩት የላቀ የሕዝብ ወገንተኝነት ዋና ጠቅላይ መምሪያው ምስጋና አቅርቧል።

የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎችና ወጣቶች ለአካባቢያቸው ሰላምና ደህንነት ቁርጠኛ በመሆን፣ የጸጥታ ሃይሉ የሚሰጣቸውን መመሪያዎች ሙሉ በሙሉ በመተግበርና ለእንግዶቹ ተገቢውን አክብሮት በማሳየት ላደረጉት ከፍተኛ ትብብር ምስጋና ተችሯቸዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አሁንም በክልሉ ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን የጀመረውን የተቀናጀ የህግ ማስከበርና የህዝብ ደህንነት የማረጋገጥ ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top