በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞችና ወረዳዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የተደረጉ የድጋፍ ሰልፎች በሰላም መጠናቀቃቸው ተገለጸ።
በአማራ ክልል በተለያዩ ዋና ዋና ከተሞችና ወረዳዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አጋርነትን ለማሳየት የተደረጉ የድጋፍ ሰልፎች ሙሉ በሙሉ በሰላማዊ ሁኔታ መጠናቀቃቸውን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ።
ሰልፎቹ በደሴ፣ በኮምቦልቻ፣ በኬሚሴ፣ በደብረ ብርሃን፣ በደብረ ማርቆስ፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን ከተሞችበምስራቅ ጎጃም ዞን ከተሞች እንዲሁም በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ጎጃም ዞን ሥር በሚገኙ ልዩ ልዩ ወረዳዎች ተካሂዷል።
ፖሊስ የሕዝቡን ደህንነት ለማስጠበቅና የትራፊክ ፍሰቱ ምቹ እንዲሆን ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በተደረገው ከፍተኛ ጥበቃ በሁሉም የሰልፍ ቦታዎች ምንም ዓይነት የፀጥታ መረበሽ ሳይከሰት ፕሮግራሞቹ በሰላም ተጠናቀዋል።
ፖሊስ ለአካባቢው ሰላምና ፀጥታ መከበር አወንታዊ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የየአካባቢው ነዋሪዎች፣ ለወጣቶችና ለሰልፉ አስተባባሪዎች ላሳዩት ከፍተኛ የሥነ-ምግባርና የትብብር ስሜት ምስጋናውን አቅርቧል።
በተጨማሪም ፖሊስ የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል።




