
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል የሚያካሂደውን የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ ዛሬ ይጀምራል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል የሚያካሂደውን ክልል አቀፍ የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ ዛሬ ይጀምራል።
ለቀጣይ ቀናት በሚቆየው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራ ላይ የሚሳተፋ የኅብረተሰብ ክፍሎችም ከተለያዩ አካባቢዎች ተጉዘው በባሕር ዳር ተገኝተዋል።
ሕዝብን ወክለው የሚሳተፉ ወኪሎች በጥዋቱ በቦታው የተገኙ ሲኾን ከቆይታ በኋላ የአጀንዳ ማሰባሰብ መርሐ ግብሩ የመግቢያ ዝግጅት ይጀመራል።
d;kg;jfh’dfz