በቅንጅታዊ የጸጥታ ግብረ-ኃይልና በህዝቡ ደጋፊነት አማራ ክልል ወደ አንጻራዊ ሰላም በመመለሱ ግዙፉ የመገጭ ግድብ ተመርቋል።
በክልሉ ተከስቶ የነበረውን የጸጥታ ችግር በጽናት በማስወገድ አካባቢውን ወደ ነበረበት አንጻራዊ ሰላም እና መረጋጋት ለመመለስ በተደረገው የተቀናጀ ጥረት ከፍተኛ ወጪ የወጣባቸው ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለምረቃ እየበቁ ይገኛሉ።
የዚሁ አንደኛው ማረጋገጫ የሆነውና በከፍተኛ የመንግስት በጀት ሲገነባ የቆየው የጎንደር መገጭ ግድብ የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልሉ የስራ ኃላፊዎች እና የአካባቢው ማህበረሰብ በተገኙበት ተመርቋል።
ይህ ከፍተኛ የልማት ምዕራፍ የሆነው የመገጭ ግድብ ምረቃ እውን ሊሆን የቻለው በፌደራልና በክልሉ የጸጥታ ሃይሎች መካከል በተፈጠረው ጠንካራ የቅንጅት ስራ እና የህዝቡን ሙሉ ደጋፊነትና አጋርነት በማስተባበር በተሰራው የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ውጤት መሆኑ ተገልጿል።
የጸጥታ አካላት እንደገለጹት ዘላቂ ሰላም እና ደህንነት ለማንኛውም ሀገራዊ ልማትና እድገት መተኪያ የሌለው መሰረት ነው ብለዋል።
የህዝቡን ንቁ ተሳትፎ በማጎልበት የተሰራው የጸጥታ ማስከበር ስራ እንደ መገጭ ግድብ ያሉ ግዙፍ የህዝብና የሀገር ሀብቶች ተጠብቀው ለፍሬ እንዲበቁና የዜጎችን የንጹህ መጠጥ ውሃ እንዲሁም የስራ እድል ጥያቄ እንዲመልሱ ማስቻሉ ተመልክቷል።
በምረቃው ወቅት መልእክት ያስተላለፉት ከፍተኛ የአመራር አካላት ህዝቡ ያገኘውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ከጸጥታ ሃይሉ ጎን በመቆም ያሳየውን አጋርነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
የጸጥታ ሃይሉም የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ በመጠበቅ መሰል ታላላቅ የልማት ስራዎች ያለስጋት እንዲከናወኑ የማስከበር ግዴታውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።



