ለህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድኑ ሊተላለፍ የነበረ የብሬን ጥይት ከባጃጅ ጋር በቁጥጥር ስር ዋለ

ለህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድኑ ሊተላለፍ የነበረ የብሬን ጥይት ከባጃጅ ጋር በቁጥጥር ስር ዋለ

በደቡብ ጎንደር ዞን ወረታ ከተማ አስተዳደር ለህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድኑ ሊተላለፍ የነበረ 2 ሺህ 549 የብሬን ተተኳሽ ጥይት በቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር መላክ ጫኔ አስወቁ።

ጥይቱ በቁጥጥር ስር የዋለው መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም ከወረታ ወደ ባህር ዳር በሚወስደው መስመር ሲንቀሳቀስ በነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ 51953 በሆነ ባለሶስት እግር ባጃጅ ተጭኖ ሲጓዝ ነው።

ተተኳሹ በወረታ ከተማ ‘ሆድ ገበያ’ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለሚገኝ የጠላት ኃይል ለማስረከብ ታቅዶ ሲንቀሳቀስ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት በሰጠው ጥቆማ መሰረት ፖሊስና ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ባደረጉት የተቀናጀ የፍተሻ ስራ ባጃጁንና ጥይቱን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።

በአሁኑ ወቅት በወንጀል ድርጊቱ ላይ የተሳተፉ አካላትን በህግ ለመጠየቅ የሚያስችል ምርመራ እየተካሄደ እንደሚገኝም ከወረታ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top