በጎንደር ከተማ ሕገወጥ የቁማር ቤቶችና ሌሎች ሕገወጥ ተግባራት ላይ እርምጃ ተወሰደ

በጎንደር ከተማ ሕገወጥ የቁማር ቤቶችና ሌሎች ሕገወጥ ተግባራት ላይ እርምጃ ተወሰደ

በጎንደር ከተማ በሕግ የተከለከሉ የቁማር ቤቶችን፣ ቤቲንግ ቤቶችን፣ የጫትና ሽሻ ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች ሕገወጥ ተግባራት በሚፈጸሙባቸው ቦታዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

አዛዥ ኮማንደር አንተነህ ቴዎድሮስጥሪ እንደገለጹት በከተማዋ ሰላምና ፀጥታን ለማስጠበቅና በሕግ የተከለከሉ ተግባራትን ለመቆጣጠር በሁሉም ክፍለ ከተሞች የተጠናከረ ቁጥጥር ተካሂዷል ብለዋል።

በዚህም በ84 የቁማር ቤቶች፣ 13 የሽሻ እና ጫት ቤቶችን ጨምሮ በድምሩ 109 ሕገወጥ ተግባራት በሚፈጸሙባቸው ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን የጎንደር ከተማ ፖሊስ አዛዥ ገልጸዋል።

እርምጃው የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ከማስጠበቅ ባለፈ ሕገወጥ ተግባራትን በመቆጣጠር ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር በከተማ ደረጃ ከተጀመረው የተጠናከረ የቁጥጥር ሥራ አካል መሆኑንም አዛዡ አብራርተዋል።

ለህብረተሰቡ ጉዳት የሚያደርሱ ሕገወጥ የቁማር፣ የቤቲንግ፣ የጫትና የሽሻ ንግድን ጨምሮ በመሰል ሕገወጥ ተግባራት የሚሳተፉ አካላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮማንደር አንተነህ አስገንዝበዋል።

ህብረተሰቡ ሕገወጥ ተግባራትን በመከላከልና ሰላምና ፀጥታን በማስጠበቅ ረገድ ለፀጥታ አካላት የሚያደርገውን የተለመደ ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር አንተነህ ቴዎድሮስጥሪ አቅርበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top