በደብረ ማርቆስ ከተማ በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ
ከፍተኛ የክልል እና የዞን የፀጥታ አመራሮች በጎጃም ቀጠና ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ እና በቅንጅት ሊከናወኑ በሚገቡ ተግባራት ዙሪያ በደብረ ማርቆስ ከተማ ውይይት አደረጉ።
በመድረኩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ ዶ/ር አማኑኤል ፈረደ፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ፣ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራሎች፣ የደብረ ማርቆስ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ፣ የምስራቅ ጎጃም ዞንና የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አመራሮች ተገኝተዋል።
ውይይቱ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ የፀጥታ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ በቀጣናው የሚሰሩ የፀጥታ ማስከበር ስራዎችን በቅንጅትና በውጤታማነት ለመምራት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።








