የሰላም አማራጭ ለሁሉ የሚበጅ መሆኑ በተግባር እየታየ ነው፣ በፋርጣ ወረዳ የነበሩ ህገ-ወጥ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪውን በመቀበል ወደ መደበኛ ህይወት ተመልሰዋል።
በአማራ ክልል ከሰሞኑ በተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ ነው። ዛሬ ደግሞ በደቡብ ጎንደር ዞን ፋርጣ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ህገ-ወጥ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።
የፋርጣ ወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኀላፊ ሃምሳ አለቃ ማሩ አድማስ እንደገለጹት፣የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎችን በማጠናከር እና ከታጠቁ አካላት ጋር ቀርቦ በመነጋገር ህገ-ወጥ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እንዲቀበሉ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
ትናንት እና ዛሬ 32 ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መቀበላቸውንም ገልጸው በቀጣይ በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እንዲቀበሉ በትኩረት እየተሠራ መኾኑን ጠቁመዋል።
የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች ከአማራ ሕዝብ ታሪካዊ ጠላት ጋር በመሥራት ዳግም ሕዝብ አንበድልም በማለት የሰላም አማራጭን መቀበላቸውን ገልጸዋል።
ማኅበረሰቡ ሰላምን ለማጽናት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝም አንስተዋል።



