የአማራ ክልል የአስተዳደር ክላስተር ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት መካሄድ ጀመረ።

የአማራ ክልል የአስተዳደር ክላስተር ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት መካሄድ ጀመረ።

በአማራ ክልል የጸጥታ ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ ውይይት መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

በመክፈቻው ላይ የተገኙት የዕለቱ ክብር እንግዳ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ አማኑኤል ፈረደ (ዶ/ር) ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የክልሉን ሰላምና ደኅንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል።

አማኑኤል ፈረደ (ዶ/ር) አክለውም የጸጥታ ተቋማት የውስጥ ቅንጅታቸውን አጠናክረው በመቀጠል የህዝቡን ሰላምና ደኅንነት በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ በሚያስችሉ አንኳር ጉዳዮች ላይ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የቀጣይ ዘመን ራዕያችን ሰላማዊ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ፍትህ የሰፈነበት፣ ሕዝቡ በመንግስት የሚተማመንበት የአማራ ክልልን መገንባት ነው ሲሉ አማኑኤል ፈረደ (ዶ/ር) አጽንኦት ሰጥተዋል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እንደገለፁት እየተካሄደ ያለው ግምገማ የተከናወኑ ተግባራትንና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በትክክል ለመመዘን የሚያስችል መስተዋት እንደሆነ አመላክተዋልል።

ሰላም የሁሉ ነገር መሠረት መሆኑን የተናገሩት እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር) ያለ ሰላም የሚታሰብ ልማትም ሆነ መልካም አስተዳደር ሊኖር እንደማይችል ገልጸዋል። በመሆኑም የጸጥታ ተቋማት በተጠናከረ ዲሲፕሊን፣ በሙያዊ ብቃት እና በሕዝባዊ ወገንተኝነት ስሜት ግዴታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመድረኩ ላይ አማኑኤል ፈረደ (ዶ/ር) በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ፣ ሌተናል ጀኔራል ጥጋቡ ይልማ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ፣ እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ብርሃኑ ጎሽም የፍትህ ቢሮ ኃላፊ፣ ኮሚሽነር ሀብታሙ ሲሳይ የማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ አቶ አስቻለው አላምሬ የሚሊሻ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተገኝተዋል።

መተጨማሪም የፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራሎች፣ የዋና መምሪያና የመምሪያ ኃላፊዎች፣ የሻለቃና የዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዦች እንዲሁም የሌሎች የጸጥታ ተቋማት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ተሳትፈዋል።

የውይይት መድረኩ በሁለት ቀናት ቆይታው ያለፈውን በጀት ዓመት ስራዎች በጥልቀት በመገምገም እና የ2019 በጀት ዓመት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የክልሉን የጸጥታ ሁኔታ ይበልጥ የማጠናከር ግብ ሰንቆ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top