ለአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ መኮንኖች እና ስትራቴጂክ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።

ለአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ መኮንኖች እና ስትራቴጂክ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።

ስልጠናው የክልሉን ሰላም ወደነበረበት ለመመለስ እና ሙያዊ ስነምግባርን የተላበሰ አሰራርን ለማዳበር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነው።

ስልጠናውን የሰጡት የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ጥጋቡ ይልማ እንደገለፁት የወታደር ስራ ውጤታማነት የሚለካው ለህዝብ ሰላምና ለሀገር ደህንነት ሲል በሚከፍለው መስዕዋትነት ነው ብለዋል።

እንደ ሌተናል ጀኔራል ጥጋቡ ገለጻ የፖሊስ ሰራዊታችን የሚሰራው ሁለንተናዊ ተግባር ‘ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ቅድሚያ መስጠት’ በሚል ወታደራዊ እሴት ውስጥ የተቃኘ መሆን ይኖርበታል ነው ያሉት።

የክልሉ ፖሊስ የጀመረውን ስኬታማና ብቁ ተቋም የመገንባት እና የሪፎርም ስራ አጠናክሮ በማስቀጠል የህዝባችንን የሰላም ችግር ለመፍታት በቁርጠኝነት እንደሚሰራም የፖሊስ አዛዡ አመላክተዋል።

የለበስነው የደንብ ልብስ እንዲሁም የተሸከምነው ማዕረግና አርማ ሀገርን እና ክቡር ሙያን የሚወክል በመሆኑ ህዝብን በቅንነት እና በፍትሃዊነት ማገልገል ያስፈልጋል ነው ያሉት።

እንደ ክልል ብሎም እንደ ሀገር የገጠመንን ውስብስብ ችግር ለመሻገር ከኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ከፌዴራል ፖሊስ እና ከሌሎች የክልል እና የፌደራል የፀጥታ መዋቅር ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

ሌተናል ጀኔራል ጥጋቡ አክለውም አቅምን በማጎልበት ራስን ማብቃትና መገምገም ለውጤታማ ስራ አይነተኛ ሚና ያለው በመሆኑ መለመድና መተግበር ያለበት በጎ ተግባር ነው ብለዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top