በባህርዳር ከተማ የተካሄደው የክረምት የአደባባይ በዓላት የመዝጊያ ፕሮግራም በሰላም ተጠናቋል።
በአማራ ክልል በርካታ አካባቢዎች ላይ በክረምት ወራት በድምቀት የሚከበሩ የአሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል፣ አሱሪቴ፣ እንግጫ ነቀላና ከሴ አጨዳ የልጃገረዶች ክልላዊ የማጠቃለያ መርሃ-ግብር በባህርዳር ከተማ ተካሂዷል።
ፕሮግራሙ ያለምንም የፀጥታ ችግር በክልሉና በፌደራል የፀጥታ አካላት ሚና በሰላም ተጠናቋል።
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ዋለልኝ ቢምረው እንደተናገሩት ፕሮግራሙ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲጠናቀቅ የከተማዋ ፖሊስ ከክልሉ እና ከፌደራል የፀጥታ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ሰርጎ ገብነትን ለመከላከል የፍተሻ ስራ በትኩረት ተሰርቷል ብለዋል።
ለፕሮግራሙ በሰላም መጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የፀጥታ አካላት እና ሰላም ወዳዱ ማህበረሰብም አዛዡ ምስጋና አቅርበዋል።






