የመንግሥትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ህገ-ወጥ ታጣቂዎች ወደ ማህበረሰቡ ተቀላቀሉ
በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ ምስራቃዊ ቀጠና ከበለስ እስከ አጣምታና መረባ አካባቢዎች በጫካ ውስጥ ሲንቀሳቀስ የቆየው የ208ኛ ኮር “የራስ ገብሬ ብርጌድ” የሰላም አማራጭን በመምረጥ ዛሬ እጁን ሰጠ።
በብርጌድ መሪው ዜናው ሃይለማርያም መሪነት የተደራጀው ይህ ኃይል፣ የሻለቃ አመራሮችንና የሻምበል መሪዎችን ጨምሮ አጠቃላይ 56 ታጣቂ አባላቱን ይዞ ወደ ሰላሙ ማህበረሰብ ተቀላቅሏል።
ቡድኑን ይዞት ከመጣው የጦር መሣሪያ ዝርዝር ውስጥ አንድ ስናይፐር፣ አንድ ብሬን እና የተለያዩ ነፍስ ወከፍ መሣሪያዎች ይገኙበታል።
የአካባቢው ህብረተሰብ እና አመራሮች ታጣቂዎቹን በደማቅ ሁኔታ የተቀበላቸው ሲሆን በስነ-ስርዓቱ ላይ የዞን፣ የመከላከያ፣ እንዲሁም የወረዳ የፀጥታና የፖለቲካ አመራሮች ተገኝተዋል።
ሰላም የሁሉ ነገር መሰረት እና የሀገር እድገት የማዕዘን ድንጋይ ነው።
ህገ-ወጥ ታጣቂ ሆኖ በጫካ መቆየት ህብረተሰቡን ከማስመረርና ለከፋ ችግር ከመዳረግ ውጭ የሚገኝ ምንም አይነት ጥቅም ስለሌለ የሰላምን አማራጭ ተቀብሎ ከቤተሰብ እና ከህብረተሰቡ ጋር በሰላም መኖር ከሁሉ የተሻለው መንገድ ነው።
አሁንም በየጫካው የሚገኙ ሌሎች አካላት ህብረተሰብን ከማሰመረርና ከማንገላታት ወጥተው ወደ ሰላማዊ ህይወታቸው በመመለስ ላለፉት ጊዜያት ያደረሱትን ጉዳት በሠለጠነ መንገድ መካስና ማህበረሰቡን መታደግ ይኖርባቸዋል።



