የአየር ወለድ ሻምበሎች በህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድን ላይ እርምጃ ወሰዱ

የአየር ወለድ ሻምበሎች በህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድን ላይ እርምጃ ወሰዱ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መርሐ-ቤቴ እና ሚዳ ወረሞ ወረዳዎች ሲንቀሳቀስ የነበረው ህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድን በአየር ወለድ ሻምበሎች መደምሰሱን የአየር ወለድ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ማትዮስ ማዴቦ አስታወቁ።

በሰሜን ሸዋ ዞን መርሐ-ቤቴ ወረዳ ገረን ቀበሌ እና በሚዳ ወረሞ ወረዳ አላባ ቢራቦ ቀበሌዎች በመንቀሳቀስ ህዝቡን ሲዘርፍ፣ ሲያስጨንቅና ህገ-ወጥ ቀረጥ ሲሰበስብ የነበረውን የጥፋት ቡድን የአየር ወለድ ሻምበሎቹ ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርምጃ መውሰዳቸውን አዛዡ ገልጸዋል።

ኮሎኔል ማትዮስ በጥፋት ቡድኑ አጠራር የ”ናደው ክፍለ ጦር” ዘመቻ ኃላፊ መኳንንት ሽመልስን ጨምሮ ከ15 በላይ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና አባላት መደምሰሳቸውን አብራርተዋል።

በተወሰደው እርምጃም የቡድኑ አባላት መማረካቸውንና መቁሰላቸውን የገለጹት አዛዡ፣ በርካታ የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎችና የመገናኛ ሬዲዮዎች መማረካቸውን አስታውቀዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top