የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ የሰው ሀብት ልማትን በማጠናከ፣ አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ ለማዘመንና አቅሙን ለመገንባት የሚያስችለውን ዕቅድ ማጽደቁን ገለፀ።

የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ የሰው ሀብት ልማትን በማጠናከ፣ አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ ለማዘመንና አቅሙን ለመገንባት የሚያስችለውን ዕቅድ ማጽደቁን ገለፀ።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ ከክልልና ከዞን የአስተዳደርና ልማት አመራሮች እና አባላት ጋር በበይነ-መረብ (ኦንላይን) የታገዘ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅና የስምምነት ሰነድ ፊርማ አካሄደ።

ዕቅዱን ያቀረቡት ምክትል ኮማንደር መላኩ ገድፈው የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ ረዳት መኮንን እንደገለጹት የተጀመሩ የፖሊስ ሪፎርም ስራዎችን ማስቀጠልና ማስፋፋት፣ የመለዮ ለባሽና የሲቪል የሰው ሀብት አስተዳደርን ማዘመን፣ የሰው ኃይል ምልመላ፣ ልማትና አቅም ግንባታን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

የፋይናንስ፣ ንብረት፣ ሎጂስቲክስና ጠቅላላ አገልግሎትን ማሳደግ፣ የጤናና ሕክምና አገልግሎትን ማሻሻል እና የቴክኖሎጂና ዲጂታል መረጃ አስተዳደርን ማስፋፋት የሚሉ በበጀት ዓመቱ ትኩረት የሚሰጣቸው ዋና ዋና ግቦች መሆናቸውን ምክትል ኮማንደር መላኩ አክለው አብራርተዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል እና የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሸነር አያልነህ ተስፋዬ ባደረጉት ንግግር የፖሊስ ተቋም የክልሉን ህዝብ ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ፣ ወንጀልን የመከላከልና የመመርመር እንዲሁም የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ትልቅ ሀገራዊና ተቋማዊ ተልዕኮ አለበት ብለዋል።

ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራሉ አክለውም ይህንን ታላቅ ተልዕኮ በብቃትና በስኬት ለማሳካት የወቅቱን የጸጥታ ሁኔታ ያገናዘበ ህጋዊ ማዕቀፍ፣ ዘመናዊ አደረጃጀት፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሎጂስቲክስና በሙያ ብቃት የተገነባ የሰው ኃይል ወሳኝ ነው ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በ2018 በጀት ዓመት ያጋጠሙ ክፍተቶችን በዘላቂነት ለመቅረፍ እና የተቋሙን የ2027 ስትራቴጂካዊ ራዕይ ለማሳካት ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል እና የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሸነር አያልነህ ተስፋዬ አብራርተዋል።

የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሸነር አብዮት ሽፈራው በበኩላቸው በተያዘው በጀት ዓመት ተቋሙ በሰው ሀብት ልማት ላይ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ አስገንዝበዋል።

ረዳት ኮሚሸነር አብዮት በማብራሪያቸው “በተለይም የምልመላ ጥራትን ማሻሻልና አቅምን መገንባት ለፖሊስ ሰራዊቱ ውጤታማነት መሠረት በመሆኑ በልዩ ትኩረት እንሰራለን” ሲሉ ተናግረዋል።

በውይይቱ ወቅት የተሳተፉ አመራሮችና አባላት በበኩላቸው በዕቅዱ ላይ ያላቸውን አስተያየት የሰጡ ሲሆን፤ በተለይም የፖሊስ አባላትን ጥቅማ ጥቅም ከመጠበቅ፣ የሥራ አካባቢን ምቹ ከማድረግ እና ከአቅም ግንባታ አኳያ በበጀት ዓመቱ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ከተሳታፊዎች ለተነሱ አስተያየቶችና ማብራሪያ ለሚፈልጉ ጥያቄዎች በየደረጃው በሚገኙ የበላይ አመራሮች በኩል ተገቢ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በመጨረሻም በበጀት ዓመቱ የተያዙትን ግቦች ሙሉ በሙሉ ለማሳካት የጋራ ቁርጠኝነት በመያዝ እና የዕቅድ ርክክብና የስምምነት ሰነድ ፊርማ ሥነ-ሥርዓት በመፈጸም ውይይቱ ተጠናቋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top