ሶስት ሚሊዮን ብር የተጠየቀበት የህፃን ልጂ እገታ ወንጀል በፖሊስ ብርቱ ጥረት ከሸፈ።

ሶስት ሚሊዮን ብር የተጠየቀበት የህፃን ልጂ እገታ ወንጀል በፖሊስ ብርቱ ጥረት ከሸፈ።

የአሰሪዎቿን ህፃን ልጅ በማገት ገንዘብ የጠየቀችው የቤት ሰራተኛ በቁጥጥር ስር መዋሏን የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

ወጣት መቅደስ ሞገስ የተባለች የቤት ሰራተኛ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቤት ሰራተኝነት ተቀጥር ከምትሰራበት ቤት ህፃን ፊዮና ሰለሞን የተባለች የሰባት ዓመት ህፃንን በማገት ወደ አማራ ክልል ጎንደር ከተማ አግታ በመውሰድ ከቤተሰቦቿ ገንዘብ ለመቀበል ስትሞክር በቁጥጥር ስር መዋሏን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር አንተነህ ቴዎድሮስ ተናግረዋል።

እንደ ኮማንደር አንተነህ ገለፃ ግለሰቧ ህፃኗን ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር ከተማ በማምጣት በከተማዋ ማራኪ ክፍለ ከተማ ዩኒቨርሲቲ ጫካ ውስጥ በተደረገ ክትትል እና ጥቆማ መያዟን ተናግረዋል።

ተጠርጣሪዋ ለጊዜው በቁጥጥር ስር ካልዋለው ግርማ ወንድአሁን ከተባለ የአክስቷ ልጅ ጋር በመሆን ወንጀሉን በመፈፀም ለህፃኗ ቤተሰቦች ስልክ በመደወል 3 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ሲሆን ከ3 መቶ ሰባ ሺህ ብር በላይ መቀበላቸውንም ኮማንደሩ ተናግረዋል።

ፖሊስ ወንጀለኛውንና ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ብርቱ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝም አዛዡ ጠቁመዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top