ሰርጎ ገብነትንና ልዩ ልዩ ወንጀሎችን በመቆጣጠር የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን የመተማ ከተማ ፖሊስ ገለፀ።

ሰርጎ ገብነትንና ልዩ ልዩ ወንጀሎችን በመቆጣጠር የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን የመተማ ከተማ ፖሊስ ገለፀ።

በምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ የመተማ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ የከተማዋን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ሚናን እየተወጣ እንደሚገኝ የፖሊስ አዛዡ ኢንስፔክተር ዳምጠው ሞላ ተናግረዋል።

ኢንስፔክተር ዳምጠው ሞላ እንዳሉት ከተማዋ ከሱዳን ጋር አዋሳኝ በመሆኗ የተለያዩ ህገወጥ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች እና የሰዎች ዝውውር፣ ህገወጥ የጦር መሳሪያ እና ተተኳሽ ዝውውር እንዲሁም የሰርጎ ገብነት ወንጀሎች በእጂጉ የሚስተዋልበት ነው ብለዋል።

እነዚህን የወንጀል ተግባራት በመከላከልና በመቆጣጠር ለከተማዋ ሰላም መስፈን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ውጤታማ ስራ መስራቱን ነው አዛዡ የተናገሩት።

አዛዡ አክለውም ከወንጀል ምርመራ ጋር በተያያዘ ባለፈው በጀት ዓመት ከ90 በላይ የክስ መዝገቦች ላይ አስፈላጊው የምርመራ ስራ ተሰርቶ ለሚመለከተው የፍትህ አካል ተልኳል ሲሉ ጠቁመዋል።

በከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ፅህፈት ቤት የወንጀል መከላከል ክፍል ኀላፊ ኢንስፔክተር አብዮት ጎሹ በበኩላቸው ወንጀሎችን በመከላከል የከተማዋን ሰላም ለማስፈን ማህበረሰቡን ያሳተፈ የወንጀል መከላከል ስራ እየተሰራ ነው።

በተሰሩ ጠንካራ የወንጀል መከላከል ስራም የእገታ፣ ስርቆት፣ ግድያ፣ ሰርጎ-ገብነት፣ የህገወጥ የሰዎችና የጦር መሳሪያ ዝውውር ወንጀሎች መቀነሳቸውንም ነው ኢንስፔክተሩ ያመላከቱት።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top