የሠላም አማራጭን የተቀበሉ ህገ-ወጥ ታጣቂዎች እጅ ሰጡ።
በሰሜን ጎንደር ዞን አዲአርቃይ ወረዳ አንጓ አከባቢ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የህገ-ወጥ ታጣቂው ቡድን አባላት
እጅ መሥጠታቸው ተገለጸ።
በ10ኛ ዕዝ የመብረቅ ክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል ስንታየሁ ሰይድ እንዳሉት በሰሜን ጎንደር ዞን አዳርቃይ ወረዳ አንጓ አካባቢ ሰላምን በማወክ የአካባቢው ስጋት የነበሩ የህገ-ወጥ ቡድኑ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ለሠራዊቱ እጅ መስጠታቸውን ተናግረዋል።
በአካባቢው ሠላምን ለማሥፈን እና አላሥፈላጊ አካሄዶች መቆም አለባቸው ብሎ በማሠብ ታጣቂዎች ወደ ሰላም እንዲገቡ በተደረገው ጥረት ቁጥራቸው 12 የሆኑ ታጣቂዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው ሠላምን መርጠው ገብተዋል።


