ህግ ማስከበርን በቴክኖሎጂ የማዘመን ጉዞ፤ በአማራ ክልል እና በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያዎች መካከል የተደረገው ፍሬያማ የልምድ ልውውጥ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እና የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሁለትዮሽ ትብብርን እና በሌተናል ጀኔራል አስራት ደኔሮ የተመራ ከፍተኛ የአመራር ልዑካን ቡድን የሁለት ቀን የባህር ዳር ቆይታን አሰመልክተው የአማራ ክልል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል እና የአስተዳደር እና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር አያልነህ ተስፋዬ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል አያልነህ እንዳመለከቱት ተቋሙ አገልግሎቱን ዘመናዊ ለማድረግና የህግ ማስከበር አቅሙን ለማጠናከር የመረጃ ቴክኖሎጂ አሰራርን እየተገበረ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራሉ አክለውም ተቋሙ አገልግሎቱን ዘመናዊ ለማድረግና የህግ ማስከበር አቅሙን ለማጠናከር የመረጃ ቴክኖሎጂን አሰራር በመተግበር ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
በተለይም የመረጃ አያያዝን በዲጂታል ስርዓት መደገፍ፣ አሰራርን ማዘመን፣ የተቋሙን የሰው ኃይል እና የሎጂስቲክስ አቅም ማሳደግ እንዲሁም ለህዝቡ ቀልጣፋና ፍትሃዊነት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ ዋና ዋና ተግባራት መከናወናቸውንም በመግለጫቸው አብራርተዋል።
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጋር የተደረገው የሁለትዮሽ የልምድ ልውውጥም ተቋማዊ አቅምን ለማሳደግና የህግ ማስከበር ስራውን ዘመናዊ ለማድረግ ትልቅ ሚና እንደሚጫወትም ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል እና የአስተዳደር እና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር አያልነህ ተስፋዬ አክለው ተናግረዋል።
በሌላ በኩል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሎጅስቲክ ዋና መምሪያ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ሰዒድ አህመድ በአጠቃላይ ጉብኝቱ ዙሪያ ለአማራ ፖሊስ ሚዲያ በሰጡት ማብራሪያ በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በሪፎርምና በዲጂታላይዜሽን ዘርፍ የተከናወኑት ተግባራት አበረታችና ለሌሎችም አርአያ የሚሆኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ምክትል ኮሚሽነር ሰዒድ አህመድ አክለውም በጉብኝቱ ወቅት የተመለከቷቸው የዘመናዊነት እና የቴክኖሎጂ ትግበራዎች የፖሊስን የህግ ማስከበር አቅም በእጅጉ የሚያሳድጉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በሁለቱ የፖሊስ ተቋማት መካከል የሚደረገው የልምድ ልውውጥና የጋራ ትብብር የፖሊስ አገልግሎትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እና የህዝብን ደህንነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
የተጀመሩ መልካም የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንዲፋጠኑ ሰላም ወሳኝ እና መተኪያ የሌለው መሰረት መሆኑን የገለጹት ምክትል ኮሚሽነር ሰዒድ የተጀመረው የልማት ጉዞ ሳይስተጎል እንዲቀጥል የከተማዋ ነዋሪዎች፣ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ለሰላም መረጋገጥ በትኩረት እና በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።






