በሌተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ የተመራ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፍተኛ ልዑክ ባህር ዳር ገባ

በሌተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ የተመራ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፍተኛ ልዑክ ባህር ዳር ገባ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ በሌተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ የተመራ ከፍተኛ የአመራር ልዑካን ቡድን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ባህር ዳር ከተማ ገብቷል።

ልዑካን ቡድኑ ባህር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርስ በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ጥጋቡ ይልማ እና በዋና ጠቅላይ መምሪያው የማኔጅመንት አባላት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

የልዑካን ቡድኑ በባህር ዳር ቆይታቸው የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ያከናወናቸውን የሪፎርም፣ የዘመናዊነት እና የዲጂታላይዜሽን ሥራዎችን፣

በክልሉ የፍትህ ተቋማት ዘንድ እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርም እና የቴክኖሎጂ ትግበራ እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም የባህር ዳር ከተማን ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴዎችና የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን በአካል ተገኝቶ የሚጎበኝ ይሆናል።

ይህ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በሁለቱ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያዎች መካከል ያለውን ልምድና ተሞክሮ የመለዋወጥ፣ የሙያዊ ትስስርን የማጠናከር እና የህግ ማስከበር አገልግሎቱን ወደ ላቀ ደረጃ የማሸጋገር አላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top