በህጻን ላይ የደፈራ ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በ23 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።

በህጻን ላይ የደፈራ ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በ23 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።

በሰሜን ወሎ ዞን ፍላቂት ገራገር ከተማ አስተዳደር በ9 ዓመት ህጻን ላይ አሰቃቂ የደፈራ ወንጀል የፈጸመው ተከሳሽ በ23 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የመቄት ወረዳ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላለፈ።

ወንጀሉ የተፈጸመው ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ልዩ ቦታው በሬው መስክ በተባለ ስፍራ ሲሆን ተከሳሽ ናስር ሙክታር አህመድ የበግ እረኛ የነበረችውን ህጻን በኃይል ወደ ባዶ ቤት አስገድዶ በማስገባት በአሰቃቂ ሁኔታ በመድፈር አካላዊና ሥነ-ልቦናዊ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።

የፍላቂት ከተማ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል የወንጀል ድርጊቱን በጥንቃቄ ሲያጣራ ቆይቶ የሰውና የሕክምና ማስረጃዎችን በማጠናቀር መዝገቡን ለመቄት ወረዳ ፍትሕ ጽሕፈት ቤት መምራቱን አስታውቋል።

ፍትሕ ጽሕፈት ቤቱም የቀረበውን ምርመራና የተከሳሽን እምነት መሠረት በማድረግ ክስ መስርቶበታል።

ጉዳዩን የተመለከተው የመቄት ወረዳ ፍርድ ቤት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ቀን በዋለው ችሎት ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ ያመነ በመሆኑ ድርጊቱ ለሌሎች አስተማሪና ተግሣጽ ይሆን ዘንድ በተከሳሽ ናስር ሙክታር አህመድ ላይ የ23 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

በምርመራ ሂደቱና ለተጎጂዋ ህጻን ድጋፍ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት የፍላቂት ገራገር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ምስጋና ማቅረቡን የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top