ያለንበትን የጸጥታና የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ተግባራትን በትኩረት መወጣት እንደሚገባ ተገለጸ።

ያለንበትን የጸጥታና የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ተግባራትን በትኩረት መወጣት እንደሚገባ ተገለጸ።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሚዩኒኬሽን ዋና መምሪያ ለአመራሮችና ባለሙያዎች የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ።

ዕቅዱ የወንጀል መከላከል ስራዎችን በህዝባዊ መሰረት ላይ ለመገንባትና የህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽነር ጀኔራል ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር የሽወርቅ ላቀው የህዝብ ግንኙነት እና ኮሚዩኒኬሽን ዋና መምሪያ የተቋሙን አገልግሎትና ገጽታ ለህዝብ በማሳወቅ፣ ህዝባዊ አመኔታን በመገንባትና የጸጥታ ማስከበር ስራዎችን በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ ኃላፊነት አለበት ብለዋል።

ረዳት ኮሚሽነር የሽወርቅ አክለውም የያዝነውን በጀት ዓመት ዕቅድ ውጤታማ ለማድረግም ግልጽ አቅጣጫ ይዞ መንቀሳቀስ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ያቀረቡት ኮማንደር መሳይ ወርቁ እንደገለጹት ዋና መምሪያው የተቋሙን ሁለገብ እንቅስቃሴዎች በመከታተልና ተገቢ የሆኑ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ወቅታዊና አስተማማኝ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ያደርጋል። ይህም በህዝቡና በጸጥታ ኃይሉ መካከል ያለውን መቀራረብ በማጠናከር የተቋሙን ቁልፍ ተግባራት በህዝብ ትብብርና ተሳትፎ ለማስፈጸም ያስችላል ብለዋል።

ፖሊሳዊ ስራዎችንና የወንጀል መከላከል እንቅስቃሴዎችን የሚገልጹ መረጃዎችን በሁሉም የህትመት፣ የኤሌክትሮኒክስና የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ለህብረተሰቡ በስፋት ማቅረብ፤

በሰራዊቱና በህዝቡ መካከል ያለውን ወዳጅነትና አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የኪነ-ጥበብ ስራዎችን ማከናወን፤

ወቅታዊና ደራሽ ሁኔታዎችን መሰረት ያደረጉ ትምህርታዊ የመድረክ ድራማዎችንና ጭውውቶችን በማዘጋጀት የህዝቡን የግንዛቤ ደረጃ ማሳደግ፤

በአለም አቀፍ፣ በሀገር አቀፍ እና በክልል ደረጃ በሚካሄዱ የተለያዩ የስፖርት ውድድሮች ላይ በመሳተፍ የተቋሙን ስም የሚያስጠሩ አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገብ የሚሉ በበጀት ዓመቱ በትኩረት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መሆናቸውን ኮማንደር መሳይ በዕቅዱ አመላክተዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በየደረጃው ያሉ መረጃዎች በፍጥነት ለህዝብ የሚደርሱበትን አሰራር ማጠናከርና የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን ማሳደግ፣ ለሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ስራዎች አስፈላጊ የሆኑ የቴክኖሎጂና የሎጅስቲክስ ግብአቶች እንዲሟሉ መጠየቅ እንዲሁም ህብረተሰቡን ከፖሊስ ጎን ለማሰለፍ የሚደረጉ ጥረቶች በጋራ ሊጠናከሩ እንደሚገባ አስተያየቶችንና ሀሳቦችን አንስተዋል።

በተጨማሪም በውይይቱ ላይ ሀሳብ የሰጡት የኮሚዩኒኬሽን መምሪያ እና የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊዎች እንደገለጹት የተቋሙን ራዕይና ግብ ለማሳካት የተጀመሩ የለውጥ ትግበራዎች በትኩረት ሊመሩ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የህዝብ ግንኙነት እና ኮሚዩኒኬሽን ስራው ውጤታማ ሊሆን የሚችለው በተዘረጋው የለውጥ አሰራር መሰረት አመራሩና ባለሙያው በተቀናጀና በተናበበ መልኩ ስራዎችን ሲያከናውኑ መሆኑን በዕቅድ ትውውቅ መድረኩ ላይ የተገኙት ኮማንደር ነጋ ድንበሩ ጠቁመዋል።

የታቀዱ የለውጥ ስራዎችን በመተግበር ረገድ ሁሉም አመራር እና አባላት የበኩላቸውን አዎንታዊ ሚና እንዲጫወቱም ኮማንደር ነጋ አሳስበዋል።

የህዝብ ግንኙነት እና ኮሚዩኒኬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ ወንዴ ለተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማጠቃለያ እንደገለጹት ያለንበትን የጸጥታ ሁኔታ እና የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ተግባራትን በትኩረት መወጣት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ወቅታዊ ሁኔታዎችን መሠረት ያደረገ ፈጣን፣ ትክክለኛና ተጽዕኖ ፈጣሪ የመረጃ ልውውጥ ማድረግ የጥራትና የስኬት መለኪያ መሆኑንም አስምረውበታል።

የታዩ ክፍተቶችን በማረም፣ ያሉትን አጋጣሚዎችና ቴክኖሎጂዎች በአግባቡ በመጠቀም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን በሙሉ አቅም ለማስፈጸም ቁርጠኛ መሆን እንደሚገባም ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ ወንዴ አጽንኦት ሰጥተው አብራርተዋል።

በመጨረሻም የመረጃ ፍሰቱን በማጠናከርና ዘመናዊ የኮሙኒኬሽን ዘዴዎችን በመጠቀም የተያዙ ግቦች ስኬታማ እንዲሆኑ የዋና መምሪያው አመራሮችና ባለሙያዎች በተቀናጀ መንፈስ እንዲሰሩ አቅጣጫ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top