የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥና የሰላም ዋስትናን ለማጠናከር በግዳጅ ቀጠና የተሰማሩ የጸጥታ ኃይሎች አፈጻጸም ውጤታማነት በጀግኖች አንደበት ሲገለጥ።

የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥና የሰላም ዋስትናን ለማጠናከር በግዳጅ ቀጠና የተሰማሩ የጸጥታ ኃይሎች አፈጻጸም ውጤታማነት በጀግኖች አንደበት ሲገለጥ።

በምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ስምሪት ላይ የሚገኙ የአድማ መከላከል ሻለቆች አባላት፣ በአስቸጋሪ የተፈጥሮ ሁኔታና በፈታኝ መልክዓ ምድር ውስጥ በመሰማራት የህግ የበላይነትንና የህዝብን ሰላም ለማረጋገጥ ህገ-ወጥ ታጣቂውን እየደመሠሡ መሆኑ ተገለጸ።

በቆራጥነት ቆመው፣ በአንድነት ተጠናክረው፣የሀገርን ሰላምና ሉዓላዊነት እንዲጠበቅ በትጋት እየሰሩ፣

የሰላም ቀን ይምጣ፣ የህዝብ ደስታ ይፈንጥቅ ብለው፣በተሰጣቸው ኃላፊነት በጽናት ከጠላት ጋር እየተፋለሙ ይገኛሉ።

የአማራ ክልል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ኦፕሬሽናል ዋና መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር አወቀ ሞትባይኖር እና የክልሉ አድማ መከላከል ፖሊስ ምክትል ዋና መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ልጅአዱኛ ሙሉጌታ፣ በምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ስምሪት ላይ የሚገኙ የአድማ መከላከል ሻለቆች ያለፈውን የ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም በየግዳጅ ቀጠናው በመገኘት ገምግመዋል።

በግምገማው እንደተገለጸው፣ የአድማ መከላከል ኃይሉ አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ፣ ብርድና ውርጭ እንዲሁም ፈታኝ መልክዓ ምድር ሳይበግራቸው ከሌሎች የክልሉና ጀግና የመከላከያ ኃይል ጋር በመቀናጀት የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት እየተወጡ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ተግባር

የአድማ መከላከል ኃይሎቹ በዞኖቹ የሚገኙ የገጠር ቀበሌዎችን ከሕገ-ወጥ ታጣቂዎች ነፃ ለማድረግና የህዝብን ሰላም ለማረጋገጥ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በትጋት እየተወጡ መሆኑ በግምገማው ተመላክቷል።

በተሰማሩበት አካባቢ የሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮችን በተቀናጀ አሠራር በመመከት፣ የህዝብን እምነትና ደህንነት ለማጠናከር በትኩረት እየሰሩ መሆኑም ተገልጿል።

የሀገርን ሰላም ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የሚከፈለው መስዋዕትነት የህዝብን ደህንነት፣ የሀገርን ሰላምና የህግ የበላይነትን ለማስፈን የሚደረገውን ትግል እያጠናከረ መሆኑም ተመላክቷል።

በቀጣይም የአድማ መከላከል ኃይሉ ከመላው የክልሉ ህዝብ ጋር ያለውን ትብብር በማጠናከርና ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር ያለውን ቅንጅት በማሳደግ በዞኖቹ የህግ የበላይነትን፣ የህዝብን ደህንነትና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ተገልጿል።

የአድማ መከላከል ኃይሉ እየከፈለ ያለው መስዋዕትነት የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክር መሆኑንም ተጠቁሟል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top