የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ አዲስ የሥራ ሹመት ሰጡ።
በዚሁ መሠረት ሌተናል ጄነራል ጥጋቡ ይልማ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሆነው ተሾመዋል።
በሌላ በኩል የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ኮሚሽነር ጄነራል ዘላለም መንግሥቴ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸው ታውቋል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ለሁለቱም ከፍተኛ አመራሮች በስራ ዘመናቸው ስኬትንና መልካም የሥራ ዘመን ተመኝቷል።


