በድጂታላይዜሽን እና በሳይበር ደህንነት ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ።

በድጂታላይዜሽን እና በሳይበር ደህንነት ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮና ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በዋና ጠቅላይ መምሪያው፣ ለሰሜን ጎጃም ዞን እንዲሁም ለባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምርያ አመራር እና አባላት በዲጂታላይዜሽንና በሳይበር ደህንነት ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠት ጀመረ።

በዕለቱ በመገኘት የስልጠናውን መርሐ ግብር ያስጀመሩት በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር አብዮት ሽፈራው እንደተናገሩት ስልጠናው ተቋሙ በበጀት አመቱ ከያዛቸው ዋና ዋና የሪፎርም ስራዎች ውስጥ አንዱ እና የመጀመሪያው መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ ረዳት ኮሚሽነር አብዮት ሽፈራው ገለጻ የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እየተገበረ ያለውን የድጅታላይዜሽን ስራ በአግባቡ የሚመራና ወደ ተግባር የሚቀይር የሰው ሀይል ማስፈለጉ የስልጠናው መሰጠት ዋና አላማ ነው ብለዋል::

ተቋሙ እየተገበረ ካለው ተቋማዊ የለውጥ ስራ ውስጥ አንዱ የሆነው የዲጂታላይዜሽንና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ትግበራ በመሆኑ የሰለጠነ እና በዕውቀት የዳበረ የሰው ሀይል መገንባት ትልቁ ተግባር ስለመሆኑም ነው ኃላፊው የጠቆሙት።

ከስልጠናው መጠናቀቅ በኋላም ሰልጣኞች ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር እና የተሻለ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማዳበር የተቋሙን የዲጂታላይዜሽን ጉዞ ማሳለጥ ይገባቸዋል ሲሉ ረዳት ኮሚሽነር አብዮት ሺፈራው አሳስበዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በዚህ በጀት አመት ከያዛቸው ዋና ዋና ዕቅዶች ውስጥ የሙያ ላይ ስልጠና አንዱ የሆነው ይህ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና በጽንሰ ሀሳብ እና በተግባር ለተከታታይ አስር ቀናት እንደሚሰጥ የጠቆሙት ረዳት ኮሚሽነር አብዮት ሽፈራው በቀጣይም በሌሎች የሙያ ዘርፎች የሚሰጥ መሆኑን አክለው ጠቁመዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top