በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ መካሄድ ጀመረ

በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ መካሄድ ጀመረ

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል።

በግምገማ መድረኩ ላይ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጀኔራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር)፣ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራሎች፣ የዋና መምሪያ ኃላፊዎች፣ የዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዦች እንዲሁም የዋና ጠቅላይ መምሪያው ስትራቴጅክ እና ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጀኔራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) እንደገለፁት ባለፈው የበጀት ዓመት የሕዝብን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት ማስመዝገባቸውን ጠቁመዋል።

ሕግና ሥርዓትን በማስከበር እንዲሁም ተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎችን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር በኩል የተከናወኑ ተግባራትን በመክፈቻ ንግግራቸው ኮሚሽነር ጀኔራሉ ዘርዝረዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና ያጋጠሙ ክፍተቶችን በዝርዝር በመገምገም ለቀጣዩ በጀት ዓመት የተሻለ ዝግጅትና የጠነከረ ዝግጁነት ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የግምገማ መድረኩ አካል የሆኑት የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ የተተገበሩ የፖሊስ ሪፎርም ውጤቶችን በሥፍራው በመገኘት ጎብኝተዋል።

በተደረገው የመስክ ምልከታም የፖሊስ አገልግሎትን ዘመናዊና ፈጣን ለማድረግ የተዘረጉ የዲጅታላይዜሽን አሰራሮችን፣ የባህር ዳር ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዲስ የቢሮ ህንፃን፣ ሞሰብ የአንድ ማዕከል ውስጥ የፖሊስ ተካቶ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን እንዲሁም የኮሚዩኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዋና መምሪያ የሥራ ክፍሎችን ተዘዋውረው ተመልከተዋል።

ከጉብኝቱ ጎን ለጎንም የግምገማው ተሳታፊዎች ተቋማዊ አካባቢን ለማስዋብና ለአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ለመስጠት በተዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ ችግኝ ተክለዋል።

የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማው በዋና ዋና የፀጥታና የልማት ግቦች ላይ በጥልቀት በመምከር ለቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ውሳኔ በማሳለፍ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top