“ፖሊስ የሕግና የሰላም ጠባቂ፤ የማህበረሰብ አለኝታ!”
የወገራ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የአቅመ ደካማ እናትን ቤት ገንብቶ አስረከበ፤ ለተማሪዎችም የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
የወገራ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት በ2018 ዓ.ም የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ-ግብር ከፖሊስ አመራሮች፣ አባላትና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር በኮሶየ አምባራስ ቀበሌ የሚኖሩ የአቅመ ደካማ እናትን መኖሪያ ቤት ሙሉ ወጪውን በመሸፈን አስገንብቶ በዛሬው ዕለት በይፋ አስረክቧል።
ጽሕፈት ቤቱ ከቤት ግንባታው በተጨማሪ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ሕፃናት ትምህርታቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲከታተሉ የሚያስችላቸውን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
በዕለቱ በተካሄደው የርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ደሳለኝ አበራ የወገራ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ሕግና ሰላምን ከማስከበር ጎን ለጎን ማህበራዊ ኃላፊነቱን በብቃት በመወጣት የሕዝብ አለኝታነቱንና ልጅነቱን በድጋሚ ያረጋገጠበት ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።
ፖሊስ መምሪያ አዛዡ አክለውም መምሪያው በወገራ ወረዳና በአምባ ጊዮርጊስ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተመሳሳይ ሰብአዊ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን አብራርተዋል።
በዚሁ መርሃ-ግብር ላይ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ለተጠቃሚዎች የብርድ ልብስ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ለተማሪዎቹም የትምህርት ቁሳቁሶችን አበርክቷል።
የወገራ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አይፈራም አያናው በበኩላቸው፤ የወገራ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት በወረዳው ከሚገኙ የመንግሥት ተቋማት መካከል በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ግንባር ቀደም በመሆን የፈጸመው ይህ አርአያነት ያለው ተግባር የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ አይፈራም አክለውም የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ለወረዳው ነዋሪዎች ላደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍና ስጦታ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

See less





