“ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ከሚሠሩ ታሪካዊ ጠላቶቻችንን ጋር በጋራ አንሠራም” የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች
በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች በትጥቅ ትግል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።
የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች የሕዝባችን ስቃይ እና እንግልት በመረዳት ሰላምን መርጠናል ብለዋል።
ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ከሚሠሩ ታሪካዊ ጠላቶቻችንን ጋር በጋራ አንሠራም ነው ያሉት። በግጭት የባከነውን ጊዜ በልማት ለማካካስ ከመንግሥት እና ከህዝብ ጎን በመሆን በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ ገልጸዋል።


