የፖሊስ ስነ-ስርዓት ክንውኖችን የሪፎርሙ አካል በማድረግ፣ ሰራዊቱ ህግን የሚያከብር፣ በስነ-ምግባር የታነፀ እና ለህብረተሰቡ አርአያ ሆኖ እንዲያገለግል እጅግ የላቀ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

የፖሊስ ስነ-ስርዓት ክንውኖችን የሪፎርሙ አካል በማድረግ፣ ሰራዊቱ ህግን የሚያከብር፣ በስነ-ምግባር የታነፀ እና ለህብረተሰቡ አርአያ ሆኖ እንዲያገለግል እጅግ የላቀ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያን ጨምሮ በሁሉም የዞን እና የወረዳ መዋቅሮች በየዕለቱ የሚከናወኑ እንደ ፖሊሳዊ ስነ-ስርዓት ቁጥጥር (የአለባበስ፣ የጺም እና የጸጉር ንጽህና)፣ የፎሌን (ሰልፍ) ቆጠራ፣ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር እና ሰንደቅ ዓላማ የመስቀል ስነ-ስርዓት የተቋሙን ዲሲፕሊን፣ ህግን የማክበር ባህል እና የባለቤትነት ስሜት ከፍ የሚያደርጉ ቁልፍ ተግባራት ሆነዋል።

ሰራዊቱ የሰልፍና የስነ-ስርዓት ልምዶችን እንደ ማህበራዊና ተቋማዊ ባህል በመቁጠሩ፣ ተቋማዊ ዲሲፕሊኑ ከፍ ብሎ የዕለት ተዕለት ስራዎቹ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ አስችሏል።

ይህ አሰራር ከወቅታዊው የተቋሙ ሪፎርም ጋር ያለው ቁርኝት፣ ለፖሊስ አባላት የሚሰጠው ጥልቅ ሙያዊ ትርጉም እንዲሁም ለህብረተሰቡ የሚያበረክተው አርያነት እጅግ ከፍተኛ ነው።

1.ከተቋሙ ሪፎርም እና ከዘመናዊ ሰራዊት ግንባታ ጋር ያለው ቁርኝት

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ህዝብን በገለልተኝነት፣ በቁርጠኝነት እና በዲሲፕሊን ለማገልገል የሚያስችለውን አጠቃላይ የሪፎርም ማዕቀፍ በመተግበር በአካሉ የዳበረ በአዕምሮው የበለጸገ ሰራዊትን በመገንባት የህብረተሰብ አገልጋይነቱን ከፍ እያደረገ ይገኛል።

ሪፎርሙ የሰመረ እና ጠንካራ ተቋም ለመገንባት የፖሊስ አባላት ከላይ እስከ ታች በአንድ መንፈስ፣ ህግ እና ትዕዛዝ እንዲመራ የሚያደርግና በየዕለቱ የሚከናወኑ ስነ-ስርዓቶች የትዕዛዝ ሰንሰለቱን ጥንካሬ በየደረጃው ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።

ፖሊስ የህዝብ ሰላም እና ፀጥታ ጠባቂ ብቻ ሳይሆን የህግ የበላይነት እና የሰለጠነ አስተዳደር ተምሳሌት እንዲሆን ወጥ የሆነ አለባበስ፣ ንጽህና እና የተባበረ አንድነት የለውጡ መገለጫዎች ናቸው።

በክልል፣ በዞን እና በወረዳ የሚገኙ ሁሉም የፖሊስ አባላት በአንድ ሰዓት እና ስነ-ስርዓት ስራቸውን መጀመራቸው የተቋሙን መዋቅራዊ አንድነት ከፍ ያደርጋል።

የአለባበስ እና የንጽህና ቁጥጥሩ በስራ ቦታ የሚታዩ ቸልተኝነቶችን በጊዜው ለማረም እና ህጎችን የማይተገብሩ አካላት ላይ ወቅታዊ አስተማሪ እርምጃ ለመውሰድ ያስችላል።

2. ለፖሊስ አባላት የሚሰጠው ጥልቅ ሙያዊ ትርጉም

ለፖሊስ የሙያ ዲሲፕሊን የህልውናው መሠረት ሲሆን፣ ለአባላቱ ከፍተኛ ስነ-ልቦናዊ ግንባታና እና ሙያዊ ፍቅር እንዲኖርም ያደርጋል።

ያለፈው ሳምንት የነበሩ ድካሞችንና ክፍተቶችን በማስወገድ፣ አዲስ ስራዎችን በሰዓት አክብሮት እና በከፍተኛ ንቃት ለመጀመር አእምሮአዊ ዝግጁነት ይፈጥራል።

ብሔራዊ መዝሙርን በመዘመር እና ሰንደቅ ዓላማን በክብር በመስቀል አባላቱ ለሀገራቸው እና ለህዝባቸው የገቡትን ቃለ ኪዳን በየዕለቱ እንዲያስታውሱ ያደርጋል።

የአለባበስ፣ የጺም እና የጸጉር ቁጥጥር ፖሊስ ሁልጊዜም በህብረተሰቡ ላይ ንጹሕ እና ማራኪ ሆኖ እንዲታይ በማድረግ የሙያ ኩራት እንዲፈጠር ይረዳል።

የፖሊስ አባላት በጋራ ሰልፍ ጊዜ ጎን ለጎን ቆመው ሲሰሩ በመካከላቸው ያለው የመተማመን እና የመረዳዳት ስሜት እንዲጨምር ያደርጋል።

ትዕዛዝን ያለማወላወል የመቀበል እና በጋራ የመንቀሳቀስ ባህልን ስለሚያዳብር በድንገተኛ አደጋዎች ሰራዊቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተደራጅቶ እንዲንቀሳቀስና አቅሙን ለመገንባት ይረደዋል።

3. ለህብረተሰቡ የሚያበረክተው አርያነት እና ህዝባዊ ትስስር

የፖሊስ ተቋም ጥንካሬ ከህብረተሰቡ ጋር ባለው ግንኙነት፣ በሚሰጠው አገልግሎትና አርአያነት ይመዘናል።

ማህበረሰቡ ፖሊሶቹን በሰርዓት ተሰልፈው፣ ንጹሕ ልብስ ለብሰው ሲያይ በሃገሪቱ ላይ ህግና ስርአት እንዳለ ትልቅ እምነት እና ማረጋገጫ እንዲኖረው ያደርጋል።

ፖሊስ በሰዓቱ ተገኝቶ ፖሊሳዊ ስነ-ስርዓቶችን ማከናወኑ ህብረተሰቡ በሥራ ቦታ የሰዓት አክብሮትን እና ሃላፊነትን ከፖሊስ እንዲማር አርአያ ይሆናል።

የተደራጀ፣ ንጹሕ እና ስነ-ስርዓት ያለው ፖሊስ ማየት የህብረተሰቡን የጸጥታ ስጋት በመቀነስ ህዝባዊ ትብብርን፣ መረጃ የመለዋወጥ ባህልን እና አጋርነትን እጅግ የላቀ ያደርገዋል።

በአጠቃላይ በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ውስጥ በየዕለቱ የሚከናወኑት እንደ ፖሊሳዊ ስነ-ስርዓት ቁጥጥር፣ የፎሌን ቆጠራ፣ ብሔራዊ መዝሙር እና ሰንደቅ ዓላማ የመስቀል ስነ-ስርዓቶች ተራ የቢሮክራሲ ልማዶች ሳይሆኑ፤ የዲሲፕሊን፣ የሀገር ፍቅር፣ የህግ የበላይነት እና የዘመናዊ ሪፎርም አንቀሳቃሽ ሞተሮች ናቸው።

ተቋሙን በብቃት፣ በስነ-ስርዓት እና በህዝብ ፍቅር ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ለማድረግ የሚደረገው ጥረት አንዱ የማዕዘን ድንጋይ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top