ኮሚሽነር ጀኔራል ዘላለም መንግሥቴ (ዶ/ር) በአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ጤና ጣቢያ የሥራ ጉብኝት አደረጉ

ኮሚሽነር ጀኔራል ዘላለም መንግሥቴ (ዶ/ር) በአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ጤና ጣቢያ የሥራ ጉብኝት አደረጉ

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጀኔራል ዘላለም መንግሥቴ (ዶ/ር) በአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በመገኘት የጤና ጣቢያውን የዕለት ተዕለት የሥራ እንቅስቃሴና የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ በቦታው ተገኝተው ተመልክተዋል።

ኮሚሽነር ጀኔራሉ በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለጹት ተቋሙ ቀደም ሲል በክሊኒክ ደረጃ ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት ወደ ጤና ጣቢያ በማሳደግ ሰፊ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

ይህንን የተጀመረውን የማስፋፊያ ጉዞ ይበልጥ ለማጠናከርና የጤና ጣቢያውን ደረጃ ከዚህ በተሻለ መልኩ ከፍ ለማድረግ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ የጤና መምሪያ የሰራዊቱን ጤና በአስተማማኝ ሁኔታ ከመጠበቅና ብቁ የሰው ኃይል ከመገንባት አኳያ እያከናወነ ያለው ተግባር ተኮር ሥራ የሚበረታታ መሆኑን የጠቀሱት ኮሚሽነር ጀኔራል ዘላለም መንግሥቴ (ዶ/ር) ተግባሩ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።

የጤና አጠባበቅ ጣቢያ ዋና ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ሔለን ፍስሃየ በበኩላቸው ተቋሙ ከክሊኒክ ወደ ጤና ጣቢያ ደረጃ ማደጉ የሕክምና አገልግሎት አሰጣጡን ጥራትና ተደራሽነት በከፍተኛ ደረጃ እንዳሳደገው ገልጸዋል።

የጤና ጣቢያው ደረጃ ማደግ ለፖሊስ ሰራዊቱ አባላትና ለቤተሰቦቻቸው ይደርስ የነበረውን እንግልትና ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ ከማድረጉም በላይ ለአካባቢው ማህበረሰብም ጭምር የሕክምና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን በር መክፈቱን አስረድተዋል።

ምክትል ኮማንደር ሔለን አክለውም ይህ የአገልግሎት አድማስ መስፋት ተቋሙ ከሌሎች የጤና ተቋማት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሠራርና ትብብር ይበልጥ እንዲያጠናክር አግዟል ብለዋል።

በጤና ጣቢያው የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች የሰራዊቱን ጤና በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅና የተጣለባቸውን ሙያዊ ኃላፊነት ለመወጣት ሌት ከቀን ተግተው እየሰሩ እንደሚገኙ የገለጹት ኃላፊዋ ለተደረገላቸው የሥራ ጉብኝትና ለተሰጣቸው የድጋፍ ማረጋገጫ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።

በመጨረሻም በጤና ጣቢያው የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች የሰራዊቱን ጤና ከማስጠበቅና የሥራ ዝግጁነትን ከመጨመር አንጻር እያሳዩት ላለው ቁርጠኝነትና የ24 ሰዓት ተጋድሎ የእውቅናና የማበረታቻ መልዕክት ተላልፎላቸዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top