በከላላ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ

በከላላ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ

በደቡብ ወሎ ዞን ከላላ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ የጦር መሳሪያዎችን ሲያዘዋውር የነበረ ተሽከርካሪ በህብረተሰቡና በፀጥታ አካላት የተቀናጀ ክትትል በቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማዋ የፀጥታ መዋቅር አስታወቀ።

ከላላ ከተማን አቋርጦ ወደ ደሴ ከተማ ሲጓዝ በነበረና ጤፍ ጭኖ ሲንቀሳቀስ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በተደረገ ጥብቅ የመረጃ ክትትልና ፍተሻ፣ በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት የጦር መሳሪያዎችም:- 9 (ዘጠኝ) ክላሽን ኮቭ ጠመንጃዎች፣7 (ሰባት) ሽጉጦች፣15 (አስራ አምስት) የ82 ሚሊ ሜትር ሞርተር ቁንቡላዎች ናቸው።

መሳሪያው በህገ ወጥ መንገድ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች እንዲዘዋወር የተደረገው የህብረተሰቡን ሰላም ለማደፍረስ ያለመ ስለመሆኑም ተጠቁሟል።

በጉዳዩ ላይ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራው እየተጣራባቸው እንደሚገኝም ታውቋል።

ፖሊስ ህብረተሰቡ የፀጥታ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ድርጊቶችን በመጠቆም እያደረገ ያለውን አጋርነት አድንቆ፤ በተለይም ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመከላከል የሚያደርገውን የተቀናጀ እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top