በባሶ ሊበን ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ህገ-ወጥ ታጣቂዎች የመንግስትን ምህረት በመቀበል እጃቸውን ሰጡ
በህገ-ወጥነት መንገድ ላይ ተሰማርተው ሲዋጉ የቆዩ እና በምስራቅ ጎጃም ዞን በባሶ ሊበን ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 12 የቡድን አባላት የመንግስትን የሰላም ጥሪ እና የምህረት አዋጅ በመቀበል ዛሬ በደብረ ማርቆስ ከተማ ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው እጃቸውን ሰጥተዋል።
የሰላምን አማራጭ በመምረጥ እጃቸውን የሰጡት እነዚህ ግለሰቦች፣ በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እና ህዝቡ ወደ መደበኛ የልማት ስራው እንዲመለስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት መወሰናቸውን ገልጸዋል።
የጸጥታና የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እጃቸውን የሰጡትን ግለሰቦች የተቀበሉ ሲሆን፣ በሰላማዊ መንገድ ወደ ማህበረሰቡ ለመቀላቀል የወሰዱትን ውሳኔ አድንቀዋል።
የቀረበውን የሰላም አማራጭ በመጠቀም ሌሎች በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎችም ወደ ሰላማዊ ህይወት እንዲመለሱ ጥሪ ተላልፏል።
ታጣቂዎቹ ይዘዋቸው የመጡት የጦር መሳሪያዎችና ትጥቆችም በፀጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ ለቀጣይ ተያያዥ ስራዎች ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ታውቋል።



