ብሔራዊ በሰው መነገድ እና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ለመከላከል የመረጃና የጥሪ ማዕከል (8797) ተጠቃሚ ይሁኑ!
ብሔራዊ በሰው መነገድ እና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል መከላከል የመረጃና የጥሪ ማዕከል በፍትህ ሚኒስቴር ተገንብቶ ስራ ላይ እንዳለ ያዉቃሉ?
ይህ ማዕከል ከአገሪቱ ከየትኛዉም አቅጣጫ የሚሰራ ነጻ የጥሪ ማዕከል ሲሆን ቁጥሩም 8797 ነው።
በዚህ የነጻ የመረጃና የጥሪ ማዕከል የሚሰጡት አገልግሎቶች፦
• በህግ መጠየቅ ያለባቸው ተጠርጣሪዎች ለህግ እንዲቀርቡ ለማድረግ ከጥሪ ማዕከሉ ድጋፍ በመገናኘት ተጎጂ ወይም ጥቆማ ሰጪ ከሀገሪቱ ማንኛውም ክፍል ጥቆማ መስጠት የሚችልበት፤
• ለተጎጂዎች የህግ ምክር፣ የስነልቦና ድጋፍ እና የአስቸኳይ እርዳታ ወደሚያገኙበት ሪፈር የሚደረግበት፤
• ስለተጎጂወች ቅብብሎሸ አገልግሎት መረጃ የሚሰጥበት፤
• ስለህጋዊ የውጪ አገር ስራ ስምሪት እና ስለነጻ የህግ ድጋፍና ተያያዥ ጉዳዮች መረጃ የሚስጥበት፤
• ከሀገር ውጭ ያሉ ዜጎችም ባሉበት ሀገር ወደሚገኝ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጋር የሚገናኙበትን ሁኔታ የሚመቻችበት፤
• በሰው መነገድ / ድንበር ማሻገር ወነጀሎች ላይ ጥቆማ በመቀበል ወደ ሚመለከተዉ የህግ ማስከበር አካላት የሚተላለፍበት ነው።
በአጠቃላይ በሰው መነገድ እና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎች በተመለከተ መረጃ የሚያገኑበት፣ ጥቆማ የሚሰጡበት እንዲሁም ለተጎጂዎች የጥበቃና ድጋፍ አገልግሎቶችን የሚገኙበትን ሁኔታ መረጃ የምታገኙበት ማዕከል በመሆኑ እናንተም ወደ 8797 ነጻ የጥሪ ማዕከል በመደወል የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሁኑ።

