ፖሊስ ምርጫው በተሳካ ሁኔታ እንዲፈፀም የጸጥታ ኃይሉ በከፍተኛ ዝግጁነት ወደ ተግባር መግባቱ ተገለጸ።
7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ እንዲፈፀም በአማራ ክልል የሚገኘው የጸጥታ ኃይል በሰው ኃይልና በሎጀስቲክስ ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ተግባር መግባቱ ታወቀ።
የክልሉ የፖሊስ ኃይል ከመከላከያ፣ ከፌዴራልና ከሌሎች የክልሉ የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት፤ በየመንገዱ፣ በየኬላውና በየሰፈሩ በቂ የሰው ኃይል በማሰማራት ቀንና ሌሊት በትጋት እየሰራ ይገኛል።
የትራፊክ ፖሊስን ጨምሮ መላው የጸጥታ አካል የትራንስፖርት እንቅስቃሴው የተሳለጠ እንዲሆንና የሕዝቡ መደበኛ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ እንዳይስተጓጎል በየተሰማራበት ቦታ ውጤታማ ሥራ እያከናወነ መሆኑ ተረጋግጧል።
ሕገ-ወጥ የታጠቁ ኃይሎች በሕዝቡ ላይ ውዥንብር ለመፍጠርና እንቅስቃሴን ለማደናቀፍ የሚያስተላልፉት መረጃ መሬት ላይ የሌለና ፍጹም የሐሰት በመሆኑ ሕብረተሰቡ ሳይደናገጥ መደበኛ ተግባሩን እንዲያከናውን አሳስቧል።
የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለሀብቶችና አሽከርካሪዎች የጸጥታ ኃይሉን አስተማማኝ ከላላ በመተማመን የተለመደውን የሕዝብ አገልግሎት ያለ ምንም ስጋት እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል።
የጸጥታ ኃይሉ የክልሉን ሰላም ለማፍረስና ምርጫውን ለመበጥበጥ የሚሞክር የትኞቹንም ሕገ-ወጥ አካላት እንቅስቃሴ ለማክሸፍና ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ በላይ በላቀ ተጠንቀቅና ዝግጁነት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።






