የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የጸጥታ ሁኔታን በተደራጀ መንገድ በማዕከላዊ መቆጣጠሪያ ክፍል ክትትል እየተደረገ ይገኛል።
ኮሚሽነር ጀኔራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) እና የዋና ጠቅላይ መምሪያው ማኔጅመንት እና የሚመለከታቸው አመራሮች የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የፓትሮል እና የደኅንነት ሁኔታ በቀጥታ እየተከታተሉ ነው።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጀኔራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) እና የዋና ጠቅላይ መምሪያው ከፍተኛ ማኔጅመንት አባላት በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለውን የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የሰላም እና የደኅንነት ሁኔታ ከቁጥጥር ክፍል (Command Room) ሆነው በቀጥታ እየተከታተሉ ይገኛሉ።
አሁን ላይ ከመቆጣጠሪያ ክፍሉ ከሚደረገው ቀጥታ ክትትል መረዳት እንደሚቻለው በሁሉም አካባቢዎች የምርጫው ሂደት በሰላማዊ እና በተረጋጋ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የምርጫው ሂደት ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ጀግናው የሀገር መከላከለያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የደህንነት ተቋማት እና የክልሉ አድማ መከላከል እና የመደበኛ ፖሊስ ሰራዊት እንዲሁም የክልሉ የጸጥታ ኃይል ማናቸውንም የጸጥታ ስጋቶች አስቀድሞ ለመከላከል ቁጥጥሩንና ፈጣን ምላሽ የመስጠት ስራውን አጠናክሮ ማስቀጠሉ ታውቋል።








