የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ 4ኛው የምርምር ሲምፖዚየም መካሄድ ጀመረ።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ 4ኛው የምርምር ሲምፖዚየም መካሄድ ጀመረ።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ “ምርምርና ፈጠራ ለተሻለ የፖሊስ አገልግሎት እና ዘላቂ ሠላም!” በሚል መሪ ቃል ለሁለት ቀናት የሚቆየውን 4ኛውን የምርምር ሲምፖዚየም ማካሄድ ጀምሯል።

በዚሁ ከፍተኛ የፖሊስ ምርምር መድረክ ላይ በሀገር መከላከያ ሰራዊት የ6ኛ ዕዝ አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ምክትል ኮሚሽነር አበበ ደለለ፣ በብርጋዴር ጀኔራል ሶፍያን መሀመድ 602ኛ ኮር አዛዥ፣ አቶ ዳንኤል ደሳለኝ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ፣ አቶ ተሾመ ዋለ የደብረማርቆስ ከተማ ከንቲባ፣ የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ስትራቴጂክ እና ከፍተኛ አመራሮች፣ አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

ከዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በዚሁ ለሁለት ቀናት በሚቆየው ሲምፖዚየም ላይ በፖሊሳዊ አገልግሎት አሰጣጥ፣ በፈጠራ ስራዎችና በዘላቂ ሰላም ግንባታ ዙሪያ ትኩረታቸውን ያደረጉ አምስት የምርምር ጽሁፎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ይደረግባቸዋል።

ይህ የምርምር መድረክ የፖሊስ ተቋምን የአሰራር ስርዓት በሳይንሳዊ እውቀትና በምርምር ውጤቶች ለማዘመን፣ የጸጥታ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመቅረፍ እና የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ በሆነ መልኩ ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ታምኖበታል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top