የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በጋራ መስራት የሚያስችል የጋራ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በጋራ መስራት የሚያስችል የጋራ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ።

የስምምነት ሰነዱን የተፈራረሙት በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የኮሚሽነር ጀነራል ፅህፈት ቤት ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር የሽወርቅ ላቀው እንደተናገሩት የስምምነት ሰነዱ የክልሉ ፖሊስ ሰራዊት ለህዝብ ሰላምና ለሀገር ደህንነት ሲባል በየግዳጅ ቀጠናው ለሚደርስበት ጉዳት በዱቤና በነፃ የህክምና አገልግሎት ማግኘት በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ ረዳት ኮሚሽነር የሽወርቅ ላቀው ገለፃ ስምምነቱ ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ ለሰራዊቱ የተሻለ ህክምና ለመስጠት እና የሁለቱን ተቋማት በጋራ የመስራት ልምድን ከፍ ያደርጋል ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም ሰነዱ የሰራዊቱን አላስፈላጊ ወጭን ከማስቀረቱም ባሻገር የክልሉ መንግስት ለሰራዊቱ ጤና በትኩረት እየሰራ ስለመሆኑም ማሳያ ነው ሲሉ ጠቁመዋል።

የአብክመ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አበበ ተምትሜ በበኩላቸው የአማራ ክልል ፖሊስ ሰራዊት አንዱ የማህበረሰብ ክፍል በመሆኑና ለህዝብ ሰላምና ደህንነት ከአካል እስከ ህይዎት መስዕዋትነት ድረስ ለሚከፍለው ዋጋ ከወጭ ነፃ እና ተመጣጣኝ በሆነ ክፍያ የተሻለ ህክምና ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ነው ብለዋል።

አቶ አበበ ተምትሜ አክለውም የክልሉ ጤና ቢሮ ከክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ጋር በትብብር መስራቱ የክልሉን ሰላም ለማስጠበቅ ሰላምን እያስከበረ ለሚገኘው የፖሊስ ሰራዊት የጤና ዋስትና ለመስጠት ያስችላል ነው ያሉት።

ጤናማና ግዳጅን በብቃት መወጣት የሚችል ሰራዊት ለመገንባት በሁለቱ ተቋማት መካከል የተደረገው ስምምነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ኃላፊው አመላክተዋል።

በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የጤና አገልግሎት መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር መሰለ ስዩም በበኩላቸው የክልሉ ጤና ቢሮ ለክልሉ ፖሊስ ተቋም ከሚያደርገው የህክምና ቁሳቁስ ባሻገር ለሰራዊቱ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት መስማማቱ የሚበረታታ ተግባር ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ይህ የስምምነት ሰነድ ፖሊስ ተቋሙ በጤናው ዘርፍ ላደረገው የሪፎርም ስራም እንደ ትልቅ ግብዓት ይሆናል ሲሉም ኮማንደር መሰለ ስዩም ጠቁመዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top