የአማራ ክልል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች በአንኮበር ወረዳ በመገኘት የአባላትን የግዳጅ አፈፃፀም ገመገሙ

የአማራ ክልል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች በአንኮበር ወረዳ በመገኘት የአባላትን የግዳጅ አፈፃፀም ገመገሙ

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ አመራሮች በሰሜን ሸዋ ዞን አንኮበር ወረዳ በመገኘት በአልዩ አምባ ቀበሌ የሚገኙ የ29ኛና የ30ኛ ሻለቃ የአድማ መከላከልና የፖሊስ አባላትን የሥራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይ የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ም/ኮሚሽነርና የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር አበበ ውቤ፣ የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ም/ኮሚሽነርና የአስተዳደር ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር አያልነህ ተስፋዬ እንዲሁም የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ንጉሴ ሞገስ ተገኝተዋል።

ከፍተኛ አመራሮቹ የአድማ መከላከል ፖሊስ የሻለቃ አዛዦች እንዲሁም ከዞንና ከወረዳ ከመጡ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን፣ የአባላቱን የምሽግ ዝግጅትና የግዳጅ አፈፃፀም ሁኔታ በቦታው ተገኝተው ተመልክተዋል።

በተጨማሪም አመራሮቹ አባላቱ ያሉበትን ወቅታዊ ሁኔታ በመገምገም ለቀጣይ ተልዕኮ የሚያግዝ የሥራ መመሪያ የሰጡ ሲሆን የጸጥታ ኃይሉ እያከናወነ የሚገኘውን ተግባር በማድነቅ አስፈላጊውን ማበረታቻ ማድረጋቸውን ከአንኮበር ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top