በቴክኖሎጂ የታገዘ ክትትል በእንጅባራ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ

በቴክኖሎጂ የታገዘ ክትትል በእንጅባራ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ

ከባህር ዳር ወደ እንጅባራ ሲጓጓዝ የነበረ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጥይት እና የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ።

ከክልሉ ብሄራዊ መረጃና ደህንነት የተገኘውን የቴክኖሎጂ ክትትል መረጃ መነሻ በማድረግ፣ በእንጅባራ ከተማ የኬላ ፍተሻ በተደረገበት ወቅት መሳሪያው ሊያዝ መቻሉ ታውቋል።

ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ገደማ በቁጥጥር ስር የዋለው ይህ የጦር መሳሪያ በአይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ተጭኖ ሲጓጓዝ የነበረ ነው።

እስከ አሁን በተደረገው የመጀመሪያ ደረጃ ፍተሻ፡

5,174 የክላሽንኮቭ ጥይቶች፣ 4 የብሬን ጥይቶች እና 3 የክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች ተገኝተዋል።

ተሽከርካሪውን ሲያሽከረክር የነበረው አዲሱ ካሴ የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደበት ይገኛል።

ተሽከርካሪው ገና ሙሉ በሙሉ ተፈትሾ ያልተጠናቀቀ በመሆኑ፣ ጥብቅ ፍተሻው ተጠናክሮ መቀጠሉን የጸጥታ አካላት ገልጸዋል።

ተጨማሪ ውጤቶች እንደተገኙም ዝርዝር መረጃውን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top