በደቡብ ጎንደር የታጠቁ ኃይሎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ገቡ

በደቡብ ጎንደር የታጠቁ ኃይሎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ገቡ

በደቡብ ጎንደር ዞን በታች ጋይንት ወረዳ በጫካ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የኃይል አባላት የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል በሰላም ወደ ህብረተሰቡ መመለሳቸው ተገለጸ።

የሰላም አማራጩን ተቀብለው የገቡት የታጣቂ ቡድኑ አባላት፣ በነበራቸው ቆይታ በትጥቅ ትግል ማንኛውንም ዓይነት ጥያቄ መመለስ እንደማይቻል መገንዘባቸውን ተናግረዋል።

አባላቱ አክለውም አሁንም በጫካ የሚገኙ ሌሎች የታጠቁ ኃይሎች ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመው ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ማንኛውም ጥያቄ በኃይል ሳይሆን በውይይት ብቻ እንደሚፈታ ያላቸውን እምነት የገለጹት ታጣቂዎች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የበደሉትን ማህበረሰብ በልማትና በሰላም ለመካስ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ሌሎች ታጣቂዎችም የሰላም አማራጭን እንዲመርጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ታጣቂዎቹ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ሲመለሱ የአካባቢው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የመንግስት አመራሮች በበኩላቸው፣ ሰላምን መርጦ ለሚመጣ ማንኛውም አካል በሩ ክፍት መሆኑንና የተመለሱት ኃይሎች ወደ መደበኛ ህይወታቸው እንዲቀላቀሉ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ገልጸዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top