በምስራቅ ጎጃም ዞን በህገ-ወጥ ታጣቂዎች ላይ የተጠናከረ እርምጃ ተወሰደ።
በምስራቅ ጎጃም ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የህገ-ወጥ ታጣቂ ቡድኖች ላይ በተወሰደ የህግ ማስከበር እርምጃ ከፍተኛ ድል መመዝገቡ ተገለፀ።
የመንግስት የጸጥታ አካላት ባካሄዱት የተቀናጀ ኦፕሬሽን በታጣቂ ቡድኑ ላይ የሰውና የቁሳቁስ ኪሳራ መድረሱን ፖሊስ አመልክተዋል።
በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ፣ በእናርጅና እናውጋው ወረዳ (ፈለገ ብርሃን ከተማ)፣ በቢቡኝ ወረዳ (ድጎ ፅዮን ከተማ እና ወይን ውሃ) የህግ ማስከበር ስራው በዋናነት ያተኮረባቸው አካባቢዎች ናቸው፦
በእነዚህ አካባቢዎች ከታጣቂ ቡድኑ ላይ በተደረገ መጠነ ሰፊ ርምጃ በርካታ የቡድኑ አባላት ሲደመሰሱ፣ ሌሎች ደግሞ ከፍተኛ ቁስለኛ ሆነዋል።
ለጥፋት ተግባር ሊውሉ የነበሩ ልዩ ልዩ የጦር መሳሪያዎች በጸጥታ ኃይሉ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
የተወሰደው እርምጃ የአካባቢውን ማህበረሰብ ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የታለመ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ በምስራቅ ጎጃም ዞን የተመዘገበው ‘አኩሪ ድል’ በህገ-ወጥ መንገድ የታጠቁ ቡድኖችን እንቅስቃሴ ለመግታትና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለማስከበር የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑ ተመልክቷል።
ማህበረሰቡ ለጸጥታ ኃይሉ እያደረገ ያለው ትብብር ለዚህ ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉም በዞኑ ፖሊስ ተገልጿል።

