የክልሉ ፖሊስ ተቋም የጀመራቸዉን የሪፎርም ስራዎች አበረታች ዉጤት እያመጡ መሆናቸዉን ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ገለፁ።

የክልሉ ፖሊስ ተቋም የጀመራቸዉን የሪፎርም ስራዎች አበረታች ዉጤት እያመጡ መሆናቸዉን ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ገለፁ።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ፤ የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ስትራቴጂ እና ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት አካሂዷል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር)፤ የክልሉ ፖሊስ ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ በተሻለ ቁመናና ዝግጁነት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀዉ ፣ ከጀግናዉ የአገር መከላከያ እና ከክልሉየፀጥታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የክልሉን ሰላም በማስጠበቅ ዉጤታማ ስራዎችን አከናዉኗል ።

በተጨማሪም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሰራዊቱ በአቅምና በስነ-ልቦና እንዲጎለብት ሰፊ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል። በተለይም አባሉ ለህዝብና ለሀገር ደህንነት ያለውን ተቆርቋሪነት በማሳደግ ረገድ ተጨባጭ ለውጦች መመዝገባቸውንና ይህም ተቋሙን ወደ ላቀ ደረጃ እንዳሸጋገረው አስረድተዋል።

ፖሊስ ዘመናዊ አሰራርን እንዲከተል በርካታ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስራዎች መከናወናቸውን የጠቀሱት ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም፣ ይህም ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት መሰረት መጣሉን ገልጸዋል።

የፖሊስ ሙያ የዲሲፕሊን መፍለቂያ እና የሐቀኝነት መገለጫ ነው ፤ በየትኛውም ሁኔታ የሚገጥሙትን ፈተናዎች በጽናትና በጥበብ በማለፍ ለሙያው ታማኝ ሊሆን ይገባል ብለዋል። በኃላፊነት ስሜት የሚሰጥ እያንዳንዱ አገልግሎት እና ለህዝብ የሚታይ እያንዳንዱ ቅንነት የፖሊስን ክብር በህዝብ ልብ ውስጥ ከፍ ያደርገዋል።

የአማራ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነርና የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር አበበ ውቤ የክልላችንን ሰላምና ደህንነት ከማረጋገጥ ባለፈ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመቅሰም ውጤታማ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

በስውርና በተደራጀ መልኩ የሚንቀሳቀሱ ወንጀለኞችን በመቆጣጠር ረገድ ተቋማችን ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረስ የሕዝባችን ትብብርና የምርመራ ክፍላችን ቅንጅታዊ አሠራር ትልቅ ድርሻ አለው።

ከድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች እስከ ተደራጁ ቡድኖች ድረስ ያሉ የደህንነት ሥጋቶችን በጋራ በመመከት፣ የክልላችንን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ የምናደርገው ጉዞ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ወንጀለኞችን ለሕግ የማቅረብና የተደራጁ የጥፋት ኃይሎችን የማምከን ሥራዎች ተጨባጭ ድሎችን እያስመዘገበ እንደሚገኝም አረጋግጠዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነርና የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው እንደገለጹት ባለፉት ዘጠኝ ወራት የምርመራ ዘርፋችንን በቆራጥነት የማዘመን ሥራ መሰራቱን ጠቅሰው የሪፎርሙ ዋና ግብም ምርመራን ከግምትና ከስሜታዊነት አውጥቶ በሳይንሳዊ ማስረጃና በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ማድረግ ነው። ይህም የፍትህ ሂደቱን ከማፋጠኑም በላይ በሕዝብ ዘንድ ያለውን አመኔታ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል።

ዕውቀት የሌለው ምርመራ የፍትሕ መጓደል ምንጭ ነው ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ የመርማሪዎችን የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የማጣራት ክህሎት ለማሳደግ ትኩረት በመስጠተ የምርመራ መዝገቦች ጥራት እንዲጨምርና በፍርድ ቤት የሚኖራቸው ተቀባይነት እንዲጎለብት በማድረግ ለውጡን በተግባር እያረጋገጥን እንቀጥላለን ብለዋል።

ምክትል ኮሚሽነር ታደስ አያሌው አያይዘውም ዘመናዊ የዲጂታል መሣሪያዎችን በመጠቀምና የሕግ የበላይነትን በማክበር፣ ይበልጥ ግልጽና ፈጣን የሆነ የፍትሕ ሥርዓት ለመገንባት በስኬት ለመቀጠልም ተጠናክረው እንደሚሰሩ ምክትል ኮሚሽነር ታደሰ ጠቁመዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነርና የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር አያልነህ ተስፋዬ በበኩላቸው ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሰራዊቱ አመለካከት ግንባታና ስርጸት ላይ ያተኮሩ ተቋሙን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገሩ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።

እንደ ምክትል ኮሚሽነሩ ገለጻ ተቋሙ ቀደም ሲል ከነበረበት የውድቀት ስጋት ወጥቶ ዛሬ ላይ ሰራዊቱ የፖሊሳዊ ስነ-ምግባር ባለቤት እንዲሆንና የዕዝ ሰንሰለቱን በአግባቡ እንዲያከብር በቁርጠኝነት ተሰርቷል ብለዋል።

ለረጅም ጊዜ ተረስተው የነበሩ የፖሊስ የሥራ ባህሎችንና ፖሊሳዊ ስነ-ምግባርን በመመለስ፣ ተቋማዊ ክብርን የማደስና የሰራዊቱን ሞራል የመገንባት ስራዎች ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል።

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና እክሎችን ከመነሻቸው ለመቅረፍ የሚያስችሉ ፈጠራ የታከለባቸው ሃሳቦችን በማመንጨት በየደረጃው ካለው አመራርና ሰራዊት ጋር ሰፊ ውይይት ተካሂዷል። በእነዚህ የጋራ ምክክሮችም ችግሮችን መፍታት የሚያስችሉ መፍትሄዎች ላይ መደረሱን ረዳት ኮሚሽነር አያልነህ ተስፋዬ አብራርተዋል።

የተቋሙን የሪፎርም ስራ መነሻ በማድረግ በሰራተኛና በስራ መካከል ያለውን ትስስር የሚያጠናክር ፍትሃዊና ውጤታማ የምደባ ስራ ተ ብለዋል። በዚህም ሰራዊቱ ለተቋሙ ያለውን ፍቅር፣ ታማኝነትና ቅንነት በተግባር እያሳየ እንደሚገኝ በመጠቆም፤ የሪፎርም ስራው ተቋማዊ ውጤታማነትን በተጨባጭ እያረጋገጠ መሆኑን ረዳት ኮሚሽነሩ በንግግራቸው አረጋግጠዋል።

የጠቅላይ መምሪያው የጽህፈት ቤት ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር የሽወርቅ ላቀው

የክልሉ ፖሊስ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሌት ተቀን ባደረገው ጥረት የታዩ ክፍተቶችን በውጤታማነት እየቀረፈ መሆኑን ገልጸው ተቋሙ የጀመራቸው የሪፎርም ስራዎች በአሁኑ ወቅት በአስተማማኝ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ይህም ህዝቡ የእለት ተእለት እንቅስቃሴውን ያለምንም ስጋት እንዲያከናውን ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።

የክልሉ ፖሊስ ከሌሎች አጋር የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የክልሉን ሰላም እያረጋገጠ መሆኑን ጠቁመው የጋራ ጥረት ስጋቶችን ቀድሞ ለመከላከልና መረጃን ለመለዋወጥ ትልቅ ሚና የተጫወተ ሲሆን የተቀናጀ ኦፕሬሽኖችን የመምራት ልምዱ ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ዋነኛ መሰረት መሆኑን አመላክተዋል።

የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግና የጸጥታ መዋቅሩን በማዘመን በትኩረት በመስራት የህዝብና የፖሊስ ግንኙነትን ይበልጥ በማጠናከር ለክልሉ ሁለንተናዊ እድገት ዋስትና የሚሆን አስተማማኝ ሰላም ለመፍጠር መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የፖሊስ ሰራዊት ዋነኛ ተልዕኮ የህዝብን ደህንነት መጠበቅና ስርዓት ማስከበር እንደመሆኑ መጠን፣ የተጣለብንን የህግ ማስከበር ኃላፊነት ያለምንም መዘናጋትና በብቃት መወጣት ይኖርብናል።

አመራሩ የተሰጠውን ተልዕኮ በሙሉ አቅም ከመፈጸም አኳያ የሚታዩበትን የአፈጻጸም ክፍተቶች በአስቸኳይ በመቅረፍ ኃላፊነትን ተቆራርጦ ከመፈጸም ይልቅ የተቀናጀና ወጥ የሆነ አሰራርን በመከተል ቀጣይ ግቦችን ማሳካት ይገባል።

በሰራዊት አባላት መካከል የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችንና ችግሮችን በዝርዝር በመለየት ዘላቂ መፍትሄ መስጠት ለስራው ውጤታማነት ወሳኝ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ያለምንም የጸጥታ ስጋት በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ በየደረጃው የሚገኘው የጸጥታ ኃይል በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜትና በቁርጠኝነት መስራት ይኖርበታል።

በሰራዊቱ ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ ማናቸውንም ችግሮች አስቀድሞ ለመከላከል በአባላት ዘንድ የማያወላውል የግንዛቤና የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲመጣ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል።

በክልላችን ሙስና እና ብልሹ አሰራሮችን በመከታተልና ወደ ህግ የማቅረብ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል የሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ተቀራርቦ መስራት እንደሚገባም ተገልፃል ።

በመጨረሻም የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ እየተጉ ለሚገኙት እና ሁለንተናዊ ድጋፎችን በማድረግ ከጎናችን ለነበሩት ፣ለጀግናዉ የአገር መከላከያ ፣ የፌደራል የፀጥታና የደህንነት ተቋማት ፣ የክልሉ ፀጥታ ሀይሎች ኮምሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ ር) በአማራ ክልል ፖሊስ ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top