የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የ2018 ዓ.ም የ9 ወር የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እያካሄደ ይገኛል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የ2018 ዓ.ም የ9 ወር የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እያካሄደ ይገኛል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ፤ የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ የዋና ክፍልና ከዚያ በላይ የሆኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ማካሄድ ጀምሯል።

በመድረኩ ላይ በዋናነት የክልሉን አንጻራዊ ሰላምና የሕዝብ ደህንነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ አበይት ተግባራት በጥንካሬና በድክመት በመመዘን፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችንም በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ ምክክሮች ይደረጋሉ።

ቀሪ የሥራ ወራትን በላቀ ውጤት ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ ስልታዊ አቅጣጫዎችና ልዩ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ይደረሳል።

ይህ ግምገማ ዋና ጠቅላይ መምሪያው በቀጣይ ወራት በሕዝብ አገልግሎትና በሕግ ማስከበር ረገድ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሲሆን፣ በውይይቱ ማጠናቀቂያም ግልጽ የሆኑ የቀጣይ የሥራ መመሪያዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top