ሳጅን አትሌት ይስማው ድሉ በግራንድ ፕሪ አትሌቲክስ ውድድር የ10 ሺህ ሜትር አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ በተካሄደው የግራንድ ፕሪ አለምአቀፋዊ የአትሌቲክስ ውድድር ላይ የአማራ ክልል ፖሊስ ባልደረባ የሆነው ሳጅን አትሌት ይስማው ድሉ በ10 ሺህ ሜትር የላቀ ድል አስመዝግቧል።

አትሌቱ በወንዶች የ10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ርቀቱን 29፡1፡79 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ አንደኛ በመውጣት ውድድሩን በድል አጠናቋል።

ይህን ተከትሎም የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ለአትሌቱና ለመላው የክልሉ ፖሊስ ሰራዊት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

ዋና ጠቅላይ መምሪያው በመልዕክቱ፤ ሳጅን አትሌት ይስማው ድሉ ያስመዘገበው ውጤት የክልሉን ፖሊስ ስምና ዝና ከፍ የሚያደርግ መሆኑን ገልጾ፣ ለተገኘው ውጤትም አድናቆቱን ችሯል።

አትሌቱ ያስመዘገበው ይህ ስኬት በክልሉ ፖሊስ ሰራዊት ውስጥ ያሉ ስፖርታዊ አቅሞችን የሚያሳይና ለሌሎች አባላትም አርአያ የሚሆን መሆኑ ተጠቁሟል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top