7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በፖሊስ ሚና እና ስነ-ምግባር ላይ ያተኮረ ስልጠና በ5 ክላስተሮች እየተሰጠ ነው።

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በፖሊስ ሚና እና ስነ-ምግባር ላይ ያተኮረ ስልጠና በ5 ክላስተሮች እየተሰጠ ነው።

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ስኬታማ እንዲሆን የፖሊስን ሚና ለማጠናከር ያለመ ስልጠና ለሁሉም የፖሊስ አመራሮችና አባላት እየተሰጠ ይገኛል።

ስልጠናው በባህርዳር፣ በጎንደር፣ በደሴ፣ በደብረ ብርሃን እና በደብረ ማርቆስ ክላስተሮች ተከፋፍሎ የሚሰጥ ይሆናል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር ጀኔራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ለስልጠናው መነሻ ይሆን ዘንድ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ፖሊስ በምርጫ ሂደት ውስጥ የሚኖረው ሚና ለሀገር ግንባታና ለዴሞክራሲ ስርዓት እድገት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ፖሊስ ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ በመሆን፣ ለህገ-መንግስቱና ለህዝብ ደህንነት ብቻ ታማኝ ሆኖ ግዳጁን መወጣት እንዳለበት ኮሚሽነር ጀነራሉ አሳስበዋል።

በምርጫ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የጸጥታ ስጋቶችን በሰለጠነና በሰከነ መልኩ በመቆጣጠር፣ የዜጎችን የመምረጥ መብትና ደህንነት ማስጠበቅ የፖሊስ ቀዳሚ ተግባር መሆኑን ኮሚሽነር ጀነራሉ በመልዕክታቸው አጽንኦት ሰጥተውበታል።

እያንዳንዱ የፖሊስ አባል በስራው ወቅት የህዝብን አመኔታ በሚያተርፍ መልኩ የላቀ ስነ-ምግባር እንዲያሳይና ህግን ብቻ ተከትሎ እንዲንቀሳቀስ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም የአማራ ክልል ፖሊስ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከደኅንነት ተቋማት እንዲሁም ከክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ጸጥታን እያስከበረ ይገኛል፤ ይሄንንም አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ይህ በ5ቱ ክላስተሮች (ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ደብረ ብርሃን እና ደብረ ማርቆስ) የሚሰጠው ሰፊ ስልጠና፣ የምርጫው ሂደት ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅና ፖሊስ በቂ ዝግጅት እንዲኖረው ለማድረግ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ይጠበቃል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top