በደቡብ ወሎ ዞን ህገወጥ ታጣቂ ቡድን ለጥፋት ተግባር ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በደቡብ ወሎ ዞን ህገወጥ ታጣቂ ቡድን ለጥፋት ተግባር ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

የሀገርን ሰላምና የሕዝብን ደህንነት ለማረጋገጥ ግዳጁን እየተወጣ የሚገኘው የ11ኛ ዕዝ አንድ ኮር፤ በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ 022 ቀበሌ ህገወጥ ታጣቂ ቡድኑ ለጥፋት ተግባር ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ።

የክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ከበደ ካኒዶ እንደገለጹት ‘ለአማራ ሕዝብ ቆሜያለሁ’ የሚለው ህገወጥ ታጣቂ ቡድን በተግባር ግን የአርሶ አደሩንና የነጋዴውን ንብረት በማስገደድ ሲዘርፍ ቆይቷል ብለዋል።

ሰራዊቱ በወሰደው የተቀናጀ እርምጃም ቡድኑ ለእንቅስቃሴው እንደ ትልቅ አቅም ይጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎች መያዛቸውን አረጋግጠዋል።

ኮሎኔል ከበደ አክለውም የእነዚህ ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋል የጥፋት ቡድኑን የሎጂስቲክስ ሰንሰለት ክፉኛ እንዳዳከመውና የመንቀሳቀስ አቅሙን እንዳገደው ገልጸዋል።

ሰራዊቱ ለሕዝብ ንብረት መከበርና ለደህንነታቸው ላሳየው ፈጣን ምላሽ አድናቆታቸውን የገለጹት የአካባቢው ነዋሪዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ ለሠራዊቱ የሚያደርጉትን የደጀንነት ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አክለው አረጋግጠዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top