የአማራ ክልል ፖሊስ አትሌት በፈረንሳይ ሜዳሊያ ተቀዳጀች

የአማራ ክልል ፖሊስ አትሌት በፈረንሳይ ሜዳሊያ ተቀዳጀች

በፈረንሳይ ሀገር በተካሄደው የሴቶች 5 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድር ላይ የተሳተፈችው የአማራ ክልል ፖሊስ የአትሌቲክስ ቡድን አባል ዋና ሳጅን የኔነሽ ሽመክት 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሯን በድል አጠናቃለች።

አትሌቷ በዓለም አቀፍ መድረክ ባስመዘገበችው በዚህ ውጤት የሀገሯንና የክለቧን ስም ከፍ ማድረግ የቻለች ሲሆን፣ በውድድሩ ማጠቃለያም የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ለመላው የክልሉ ፖሊስ ሰራዊት አትሌት ዋና ሳጅን የኔነሽ ሽመክት ባስመዘገበችው ውጤት የተሰማውን ኩራት ገልጿል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top