በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የህገ-ወጥ ታጣቂው አባላት እጃቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።

በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የህገ-ወጥ ታጣቂው አባላት እጃቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።

የሀገርን ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው፣በሕገ-ወጥ የትጠቅ እንቅስቃሴ ውስጥ የቆዩ በርካታ አካላት እጃቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ ።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ በሚገኙ ገደብጌና አካባቢው በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 60 ህገ-ወጥ ታጣቂዎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ሰላማዊ ህይወት መመለሳቸው ተገልጿል።

የወገራ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው፣ የሰላም አማራጭን ተቀብለው ወደ ህብረተሰቡ ከገቡት 60 ህገ ወጥ ታጣቂዎች ውስጥ 45ቱ የታጠቁ ሲሆኑ፣ 15ቱ ደግሞ ጀሌዎች መሆናቸውን ገልጿል።

በግጭት ውስጥ የቆዩት እነዚህ ታጣቂዎች የሰላም አማራጩን ተቀብለው መመለሳቸው በአካባቢው ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን፣ የሕዝቡን ደኅንነት ለማረጋገጥና የልማት ሥራዎችን ለማፋጠን ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተጠቅሷል።

የኅብረተሰቡን ሰላም ለማስፈንና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ጥምር ጦሩ በከፍተኛ ቁርጠኝነትና የኃላፊነት ስሜት እየሰራ መሆኑ ተጠቁሟል።

በሕገ-ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው የሀገርንና የሕዝብን ሰላም እያወኩ ያሉ አካላት የሰላም አማራጭን በመምረጥ ወደ ሰላማዊ ሕይወታቸው ሊመለሱና የበደሉትን ሕዝብ ሊክሱ እንደሚገባም ጥሪ ቀርቧል።

ጥምር ጦሩም ሕግ የማስከበርና የሕዝብን ደኅንነት የማረጋገጥ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top