የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት የወንጀል መከላከልንና የሰላም ማስጠበቅን እያጠናከረ መሆኑ ተገለጸ።

የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት የወንጀል መከላከልንና የሰላም ማስጠበቅን እያጠናከረ መሆኑ ተገለጸ።

በደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ስር የሚገኙት የ2ኛ እና 3ኛ ፖሊስ ጣቢያዎች ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ባከናወኗቸው የሰላምና የፀጥታ ሥራዎች አበረታች ውጤቶችን እያስመዘገቡ እንደሚገኙ ተገለጸ።

የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ከህዝቡ ጋር ያለውን ትብብር በማጠናከር ወንጀልን አስቀድሞ በመከላከል ረገድ የላቀ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ ሆነዋል።

ህብረተሰቡ የፀጥታ ተግባራትን ሙሉ በሙሉ በባለቤትነት በመመራት በቀንም ሆነ በሌሊት አካባቢውን ተደራጅቶ በመጠበቅ ሰላሙን በጽናት እያስጠበቀ ይገኛል።

በተለይም ከታላቁ የግሼን ማርያም በዓል የተመለሱ እንግዶችን በአግባቡ በመቀበል፣ በማስተናገድና ደህንነታቸውን በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል።

አካባቢውን ከማረጋጋት ባሻገር፣ ህብረተሰቡና የፀጥታ ኃይሉ በመቀናጀት አጠራጣሪ አካላትን (ጸጉረ-ልውጦችን) በንቃት በመከታተልና በመቆጣጠር ሰላም እና ፀጥታን አስተማማኝ ማድረግ ተችሏል።

የፀጥታ ኃይሉና የህዝብ ጥበቃው ዛሬም በከፍተኛ ንቃትና ቁርጠኝነት የዕለት ተዕለት የጥበቃ ሥራውን እያከናወኑ ይገኛሉ።

ይህ ተግባር ማህበረሰቡ ሰላምን የሚሻና ለኑሮው መረጋጋት ቀዳሚውን ቦታ የሚሰጥ መሆኑን በግልጽ ያሳያል።

የህዝብና የፀጥታ አካላት አብሮነት የትኛውንም ፈተና ሰብሮ ማለፍ የሚያስችል አቅም የሚሰጥ በመሆኑ፣ መሰል መልካም ተሞክሮ፣ በሌሎች አካባቢዎችም ተጠናክሮ ሊቀጥልና ሊተገበር ይገባል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top