በከተማዋ ሰላማዊ የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲኖር ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ፖሊስ ገለፀ።

በከተማዋ ሰላማዊ የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲኖር ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ፖሊስ ገለፀ።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ በከተማዋ ሰላማዊና የተሳለጠ የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲኖር በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

በከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ዋና ክፍል ኀላፊ ኮማንደር ብርሃን ተቀባ እንደተናገሩት በከተማዋ የትራፊክ አደጋን በመቀነስ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር የግንዛቤ ፈጠራ ስራ፣ የመንገድ ዳር የትራፊክ መብራቶች ጥገናና ጥብቅ የሆነ የቁጥጥር ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ባለፈው 2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በሰውና በንብረት ላይ የደረሱ የትራፊክ አደጋዎች መቀነሳቸውን የጠቆሙት ኃላፊው ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመትም የትራፊክ ፍሰቱን ጤናማና ሰላማዊ በማድረግ አደጋን ለመከላከል በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት።

በተያዘው በጀት ዓመትም ከመንገድ ትራንስፖርት እና ከከተማዋ ወጣቶች ጋር በቅንጅት በመሆን ለአሽከርካሪዎች፣ ለተማሪዎች እና ለልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ስለትራፊክ አደጋ አስከፊነት፣ በመንገድ አጠቃቀምና በትራፊክ ህግና ደንብ ዙሪያ ግንዛቤ በመስጠት አደጋዎችን በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ እንደሚሰራም ኃላፊው አመላክተዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top